Tender Detail

Tender Details

  • Company በመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ምስራቅ ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የጊንር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
  • Address ደቡብ ክልል ኢትዮጵያ, Phone: 0226641320
  • Website
  • Deadline22 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-09-19 00:00:00
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

በመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ምስራቅ ሪጅን ጊንር ቅ/ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ቤት ለ5 ዓመት አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡

በመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ምስራቅ ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የጊንር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


                                                                        የቢሮ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ 

በመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ምስራቅ ሪጅን ጊንር ቅ/ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ቤት ለ5 ዓመት አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፦ 

1ኛ የግብር ከፋይነት የምዝገባ የምስከር ወረቀት፣ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ፣ የዘመኑን ግብር የከፈለበት ማስረጃ ማያያዝ የሚችልና የስልክ፣ውሃ፣ መብራት እና በቂ መጸዳጃ ቤት ያለው፡፡ 

2ኛ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ብር 100 (አንድ መቶ) ብር በመክፈል ከጊንር ቅ/ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ፡፡ 

3ኛ ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ የአንዱ ካ.ሜ (ካሬ ሜትር) ዋጋ ቫትን ጨምሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የቤቱ ስፋት 300 ካ.ሜ (ካሬ ሜትር) እና የግቢ ስፋት 500 ካሬ በላይ ቢሆን ይመረጣል ፡፡ 

4ኛ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦሪጅናል እና ኮፒ በማድረግ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 

5ኛ የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 16ኛው ቀን የጨረታ ሰነዱን አሪጅናል እና ኮፒ በማድረግ አሽገው እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዳቸውን ጊንር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው የሚከፈተው አዲስ አበባ ባለው ዋና መስሪያ ቤት በመሆኑ አሸናፊው ሲለይ ውል ለመፈጸም ዝግጁ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

 6ኛ ሪጅን ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ለጨረታው ያሸነፉበትን ለቢሮ የሚሆን ቦታውን የሚገልጽ መረጃ የመስጠት ግዴታ አለባቸው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0226641320/21 ደውለው መጠየቅ ይኖርባቸዋል፡፡

                    በመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ምስራቅ ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የጊንር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

Save Tender