Tender Detail

Tender Details


አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 103/1990 እና በማሻሻያ አዋጅ 807/2005 መሰረት የካፒታል እቃ ፋይናንስ ስርዓት ለማቅረብ የተቋቋመ እና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንከ የስራ ፈቃድ የተሰጠው የፋይናንስ ተቋም ሲሆን ቦሌ ከ/ከተማ ቡልቡላ ሳይት ብሎክ 8 የቤት ቁጥር 204 እና 205 የንግድ ቤቶችን በጨረታ አወዳድሮ የተሻለ ዋጋ ላቀረቡ ተወዳዳሪዎች ለማከራየት ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ጋብዘናል።


                                                                         የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

                               የጨረታ መለያ ቁጥር የንግድ ቤት ኪራይ 1/2017

አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 103/1990 እና በማሻሻያ አዋጅ 807/2005 መሰረት የካፒታል እቃ ፋይናንስ ስርዓት ለማቅረብ የተቋቋመ እና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንከ የስራ ፈቃድ የተሰጠው የፋይናንስ ተቋም ሲሆን ቦሌ ከ/ከተማ ቡልቡላ ሳይት ብሎክ 8 የቤት ቁጥር 204 እና 205 የንግድ ቤቶችን በጨረታ አወዳድሮ የተሻለ ዋጋ ላቀረቡ ተወዳዳሪዎች ለማከራየት ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ጋብዘናል።

  1.  ተጫራቾች ተወዳድረው ባሸነፉበት የንግድ ቤት ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ለማውጣት፣ ቤቱን ተከትሎ ማህበራዊ ወጭዎች ማለትም የተጠቀሙበትን የውሀ እና የመብራት ፍጆታ ወጭዎችን ለመክፈል ፈቃደኛ የሆኑ እና የነዋሪዎችን ሰላም የማያደፈርስ ስራ ለመስራት ፍቃደኛ መሆን አለባቸው፡፡ 

  2. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የንግድ ቤት የጨረታ ማስከበሪያ 5,000 (አምስት ሺ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

  3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 9/01/2018 ዓ.ም የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ፒያሳ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ወደ 6 ኪሎ መሄጃ ድንበሬ ህንፃ ጎን በሚገኘው አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ ኢማ ዋና መስሪያ ቤት 5ኛ ፎቅ ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡ 

  4. ተጫራቾች የጨረታ ፋይናሽያል ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ እስከ 9/01/2018 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 

  5.  ጨረታው በቀን 09/01/2018 ዓ.ም በ4፡00 ተዘግቶ በእለቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ ኢ.ማ ዋና መ/ ቤት ህንጻ 4ኛ ፎቅ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል። 

  6.  ኩባንያው ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። 

አድራሻ፡- ፒያሳ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ወደ 6 ኪሎ መሄጃ ድንበሬ ህንፃ ጎን

           ለበስጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 011-1-26-38-88 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ። 

                                                               አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አ.ማ                         

Save Tender