የደ/ብርሃን ከተማ ውሃና ፍሳሽ ድርጅት ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የደንብ ልብስ ተሰፍቶ ለ226 ሰራተኛ ፣ ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያ፤ ሎት 3 የቧንቧ መገጣጠሚያ፣ ሎት 4 የኤሌትሪክ እቃ፤ ሎት 5 የላብራቶሪ እቃ ሎት 6 ፈርኒቸር፤ ሎት 7 ኮምፕውተር እና ፕሪንተር በዘርፉ ከተሰማሩ ንግድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የደ/ብርሃን ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 0003/2018
የደ/ብርሃን ከተማ ውሃና ፍሳሽ ድርጅት ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የደንብ ልብስ ተሰፍቶ ለ226 ሰራተኛ ፣ ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያ፤ ሎት 3 የቧንቧ መገጣጠሚያ፣ ሎት 4 የኤሌትሪክ እቃ፤ ሎት 5 የላብራቶሪ እቃ ሎት 6 ፈርኒቸር፤ ሎት 7 ኮምፕውተር እና ፕሪንተር በዘርፉ ከተሰማሩ ንግድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር ለሚፈልጉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ የንግድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቲን ነምበር ሰርተፊኬት ያለው የግዥ መጠኑ 200,000 /ሁለት መቶ ሺ ብር/ እና ከዚያ በላይ የሚሆን ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነና የዘመኑን ግብር ማስረጃ ለመክፈላቸው አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ ኦርጅናሉንና ኮፒ ለየብቻው በታሽገ ፓስታ የአንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል በመሙላት ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣ የድምር ስህተት ካለ በአንድ መስመር በመሰረዝ ፖራፍ በማድረግ የተስተካከለውን በምርመራ አምድ ላይ በትክክል መሙላት ይጠበቅባቸዋል፣
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ እስከ 5፡00 በስራ ሰዓት የተዘጋጀው ሰነድ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በደ/ብ/ከ/ው/ፍ/አ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁ/2 በመቅረብ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፣
- የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ድረስ በ3፡29 ሰዓት ክፍት ሆኖ በዚሁ ቀን 3፡30 ይታሸጋል። በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡00 ሰዓት የደ/ብ/ከ/ው/ፍ/አ/ድርጅቱ በአዳራሽ ውስጥ ይከፈታል የመክፈቻው ቀን በዓል ላይ ከዋለ በማግስቱ ይከፈታል፡፡
- የጨረታውን ማስከበሪያ ተጫራቾች የተጫረቱበትን የጠቅላላ ዋጋ 1% በማስላት በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል ሆኖም በጥሬ ገንዘብ የሚያስይዝ ተጫራች ያስያዘበትን የገንዘብ መቀበያ ሰነድ ኮፒ በማድረግ በጨረታ ሰነዱ አሽጎ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣
- አሸናፊው የሚለየው በነጠላ ዝቅተኛውን በማወዳደር ሆኖ የተሞላው ዋጋ ከወቅቱ ገበያ ጥናት በላይ ከሆነ ውድቅ ይደረጋል፤
- አሸናፊው ድርጅት ወዲያውኑ ውል ይፈጽማል የውል ማስከበሪያ በአሸነፈበት የጠቅላላ ዋጋ ብር 10% ያሲዛል፣
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ማሻሻያ ማድረግ ወይም እራሳቸውን ከጨረታው ማግለል አይችሉም፣
- ተወዳዳሪዎች እራሳቸውን ከጨረታው ማግለል ቢፈልጉ ጨረታው ከመታሸጉ በፊት ማመልከቻ በመፃፍና ሳጥን ውስጥ በማስገባት ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል ይችላሉ፣
- አሸናፊው ተጫራቾች ያሸነፋበትን እቃ በራሱ ወጪ ደ/ብ/ው/ፍ/አገ/ጽ/ቤት ቢሮ ማድረስ ይጠበቅበታል፣
- አሸናፊው ድርጅት መ/ቤቱ በጠየቀው እስፔስፊኬሽን መሠረት እቃውን ማቅረብ ይኖርበታል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሚገዙበት ወቅት ለቧንቧ መገጣጠሚያ ግዥ ውሃ አገልግሎቱ ያስቀመጠውን ሳንፕል ማየት ይጠበቅባቸዋል፣
- መ/ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ ጨረታውን 25% በመጨመርና በመቀነስ ማሻሻል ይችላል፣
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች በድርጅቱ ቴክኒክ ኮሚቴ ጥራቱ ተገምግሞ ትክክል ሆኖ ሲረጋገጥ ክፍያ ሚከፈል ይሆናል ወይም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በኢትዮጱያ ጥራትና ደረጃዎች ኤጀንሲ መ/ቤቱ የሚያስመረምር ሲሆን የምርመራ ወጪውን አሸናፊው ድርጅት ይከፍላል፣
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታ ሰነድ ወይም የጨረታ ዋጋ ፀንቶ እሚቆየው ጨረታው ከተፈከተበት ቀን አንስቶ ለ45ቀናት የፀና ይሆናል፡፡
- አንዱ በሌላው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፣
- ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011-681-70-23 መጠየቅ ይችላሉ
የደ/ብርሃን ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
