በአሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የሃባቦ ጉዱሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 ዓ.ም የተለያዩ የጽሕፈት መሳሪያዎችን፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸሮች፣ የደምብ ልብሶች፣ ጎማዎች እና ሌሎች መሳሪያዎችን ከመንግስት በተገኘ በጀት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በአሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የሃባቦ ጉዱሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 ዓ.ም የተለያዩ የጽሕፈት መሳሪያዎችን፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸሮች፣ የደምብ ልብሶች፣ ጎማዎች እና ሌሎች መሳሪያዎችን ከመንግስት በተገኘ በጀት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እንዲሁም ከሚመለከተው የገቢዎች ጽ/ቤት ግብር ስለመክፈላቸው የድጋፍ ደብዳቤ የምስክር ወረቀት (clearance) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በገንዘብ ሚ/ር በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው።
- የጨረታውን ሰነድ በደዱ ከተማ ሃባቦ ጉዱሩ ወረዳ የገቢዎች ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ከፍለው ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 ከሰዓት 7፡30 እስከ 11፡30 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የተጫረቱበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ከቴክኒካል ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች (TIN) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደረባቸው ዕቃዎች ዋጋ ከቫት ጋር (With VAT) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የገዙትን ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ቀናት በደዱ ከተማ በሃባቦ ጉዱሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቁጥር 1 ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ15ኛው የስራ ቀን 10፡00 ተዘግቶ በ16ኛው የስራ ቀን ጠዋት 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደዱ ከተማ በሃባቦ ጉዱሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቁጥር 11 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃ የሚያቀርቡት በደዱ ከተማ በሃባቦ ጉዱሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ይሆናል።
- የቴክኒካልና (technical) በኦሪጅናልና በኮፒ ፋይናንስ (finance) ዶክመንት በኦሪጅናልና በኮፒ በሰም ታሽጎ በአንድ ፖስታ መቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች በፖስታው ጀርባ ላይ የራሳቸውን ማህተም፤ አድራሻና ስልክ ቁጥር መጻፍ አለባቸው፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለተጨማሪ መረጃ ከዚህ በታች በተዘረዘሩ ስልክ ቁጥሮች ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡ 0917032905/0910794653
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የሃባቦ ጉዱሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
