የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 10 የተለያዩ የሲቪል ግንባታ ሥራ ለኮንስትራከሽን ስራዎች የሚውል በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ በተዘጋጀው መደበኛ የጨረታ ሰነድ መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Petroleum Supply Enterprise(EPSE) (የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 005/2018 9.
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 10 የተለያዩ የሲቪል ግንባታ ሥራ ለኮንስትራከሽን ስራዎች የሚውል በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ በተዘጋጀው መደበኛ የጨረታ ሰነድ መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት የሚችሉ ደረጃ 6 እና ደረጃ 7 የሆኑ ሥራ ተቋራጮች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቶች የሚከተሉትን ሠነዶች ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት (VAT)፣የግብር ከፋይነት ሠርተፍኬት (TIN)፣የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና ስለ ግብር አከፋፈል የተሰጠ ማስረጃ
- በተ.ቁ 1 ከተጠቀሱት በተጨማሪ ተጫራቾች ደረጃቸውን የሚገልጽ የታደሰ የምስከር ወረቀት፣ ለሥራው የሚያስፈልጉ መሣሪያዎችና ተሽከርካሪዎች ዝርዝር መግለጫ፤ለሥራው የሚያስፈልጉ የባለሙያዎች መግለጫና ዝርዝር እና በጨረታው ለተጠየቀው ሥራ ወይም ተመሳሳይ የሥራ ልምድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቶች ብር100,000.00 የጨረታ ማስከበሪ (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ ቼh (CPO) ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለግንባታ ስራው አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ የመወዳደሪያ ሰነድ በታሸነ ኢንቨሎፕ እስከ 6/1/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 602 ለዚህ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በዚሁ ቀን 6/1/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4:05 ሰዓት ተጫራች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 602 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሥራውን ዓይነትና ሁኔታ በአካል በመገኘት ማየትና ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመከፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ከድርጅቱ ግዥና ትራንስፖርት ከፍል ቢሮ ቁጥር 011 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሣርቤት በሚወስደው መንገደ 300 ሚትር ዝቅ ብሎ
ስልክ ቁጥር 011-551-32-88
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት
