በን/ስ/ላ/ከ/ከተማ ለቡ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን እቃዎች ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
ለቡ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዢው መለያ ቁጥር 01/2018
በን/ስ/ላ/ከ/ከተማ ለቡ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን
ሎት1: አላቂ የቢሮ እቃዎች - የሲ.ፒ.ኦ መጠን 4000
ሎት2: ቀሚ እቃዎች- የሲ.ፒ.ኦ መጠን 4000
ሎት3: የትምህርት እቃዎች- የሲ.ፒ.ኦ መጠን 3000
ሎት4: የጽዳት እቃዎች- የሲ.ፒ.ኦ መጠን 4000
ሎት5: የደንብ ልብስ - የሲ.ፒ.ኦ መጠን 2000
ሎት 6 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች- የሲ.ፒ.ኦ መጠን 3000
ሎት 7 የፈርኒቸርና ኤሌክትሮኒከስ ጥገና አገልግሎት — የሲፒ.ኦ መጠን 5000
ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት፤
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብርየከፈሉ፣ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒአ ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 150 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ለቡ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 2-02 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ10 የሥራ ቀናት በለቡ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 2-02 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛው ቀን በ11፡30 ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ለቡ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 2-02 ይከፈታል፡፡ የመከፈቻ ቀኑ ቅዳሜ ና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎት 1፣ ሎት 2፣ ሎት 3 እና ሎት 4 ናሙናማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለሎት 2 እና ለሎት 5 በቀረበው የፍላጎት መግለጫ መሰረት የተሟላ የፍላጎት መግለጫ ማዘጋጀትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
- የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ፡- ስልክ ቁጥር፡- 0111-4-71-31-90/91
አድራሻ፡- ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 01 ሃይሌ ጋርመንት ሃጫሉ መንገድ ኖክ ማደያ ጀርባ ለቡ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ለቡ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
