የምስራቅ ሐረርጌ ዞን የኮምቦልቻ ወረዳ ፍርድ ቤት ለሥራ የሚውሉ የለያዩ ዕቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የምስራቅ ሐረርጌ ዞን የኮምቦልቻ ወረዳ ፍርድ ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የምስራቅ ሐረርጌ ዞን የኮምቦልቻ ወረዳ ፍርድ ቤት ለሥራ የሚውሉ የለያዩ ዕቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተገለጹትን ዕቃዎች ማቅረብ የሚችሉትን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. የተለያዩ ቋሚ ዕቃዎች
2. የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች እና የመኪና ዕቃና ጎማዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን የጨረታ መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይፈልጋል፡፡
ተወዳዳሪዎች ማቅረብ ያለባቸው-
1. በዘርፉ በተሰማሩበት ሥራ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር ከፍለው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
2. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ማስከበሪያ ጠቅላላ ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ ፣ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ብር በቢሮ ስም አሰርተው ማቅረብ የሚችሉ
3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. የግብር ከፋዮች ቁጥር /ቲን ያላቸው እሴት ታከስ 15 ፐርሰንት ቫት ተመዝጋቢዎች መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
5. ተጫራቾች ጨረታ ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ወደ ኮምቦልቻ ወረዳ ፍርድ ቤት ቢሮ ግቢ ማቅረብ የሚችሉ
6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 21 ቀናት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከኮምቦልቻ ወረዳ ፍርድ ቤት ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
7. የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ23ኛው ቀን አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ29ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በእለቱ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
8. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0913893337/0954035123/0937503917/09137 46418 ደውለው ወይም መ/ቤታችን ድረስ በጽሑፍም ሆነ በአካል ቀርበው መረዳት ይችላሉ፡፡
የምስራቅ ሐረርጌ ዞን የኮምቦልቻ ወረዳ ፍርድ ቤት
