Tender Detail

Tender Details

በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 6 አስተዳደር ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በ1ኛ ዙር ጨረታ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የጽህፈት መሳሪያ፤ የጽዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ ልዩ ባህሪ ያላቸው የመስተንግዶ አገልግሎት፣ የመኪና ኪራይ፣ የትራንስፖርት መኪና ኪራይ፣ የጉልበት/የጭነት አገልግሎት፣ ህትመት፣ ዲኮር፣ የኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ላፕቶፕ፣ ፎቶ ኮፒ ማሽን ስፔር ፖርት ግዢ እንደገና የኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ላፕቶፕ፣ ፎቶ ስፔርፖርት ማሽን ጥገና፣ የመኪና ጎማ፣ እና አነስተኛ ሞንታርቦ በ1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድረን መግዛትና ማሰራት እንፈልጋለን።

በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 6 አስተዳደር ጽ/ቤት

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር-01/2018

በዚህ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

1. በዘርፍ አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የከፋይነት መለያ ቁጥር ቲን ነምበር፣ የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ያላቸው።

2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣

3. ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የአራዳ ከፍለ ከተማ ወረዳ 6 ፋይናንስ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ።

4. በተጨማሪ ተጫራቾች የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን/ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

5. በጨረታው ላይ ያወጣናቸውን እቃዎች በሙሉ ኦሪጅናል እና ጥራታቸውን የጠበቁ ሆነው ማቅረብ የሚችሉ።

6. ተጫራቾች የጨረታ ፖስታ በሚያስገቡበት ጊዜ ለተወዳደሩበት ዕቃ ሳምፕል ከሰነዱ እኩል ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት መ/ቤቱ ድረስ ማምጣት ይኖርባቸዋል።

8. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ ብቻ የሚወዳደሩበትን ቫት በመጨመርና በእያንዳንዱ ገጽ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም በማኖር በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ተከታታይ የስራ ቀናት በተጠቀሰው ቢሮ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ኮፒና ኦሪጅናል ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9. የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ ማቅረብ አለባቸው።

10. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸውን ዕቃዎች አጠቃላይ ዋጋ 10 % የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከጽ/ቤቱ ጋር የግዢ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖባቸዋል።

11. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ11ኛው የስራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ የጨረታው አከፋፈት ላይ ለመገኘት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን /በ11ኛው/ የስራ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት በወረዳው አስተዳደር አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡

12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጫራቾች ለሳምፕል /ለናሙና ማቅረቢያ የሚያገለግላቸውን በተጫራቹ ድርጅት ቅጽ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

አድራሻ፡- የካቲት 12 ሆስፒታል ጀርባ በሚገኘው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መንገድ ይዞ ከኢትዮጵያ

የእይነ ስውራን ማህበር ፊት ለፊት በሚገኘው በአራዳ ከፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር

ስልክ ቁጥር፡- 0111262899/0111580697

በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 6 አስተዳደር ጽ/ቤት

Save Tender