Tender Detail

Tender Details

  • Company Agape Saving and Credit Cooperative (አጋፔ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር)
  • Address ለሚ ኩራ ከፍለ ከተማ ወረዳ 13 ፖሊስ ጣቢያ አጠገብ ኢምፔሪያል ህንጻ 2ኛ ፎቅ ላይ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09 06-56 22 22
  • Website
  • Deadline09 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price50.00
  • Bid Security2%
  • opening date2025-09-10 00:00:00
  • Categories Accounting & Auditing , Finance

በለሚኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የሚገኝ የአጋፔ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/ህ/ስራ ማህበር የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የስራ እንቅስቃሴ ሂሳብ ባለሙያ አወዳድሮ ለማስመርመር ይፈልጋል።

Agape Saving and Credit Cooperative (አጋፔ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በለሚኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የሚገኝ የአጋፔ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/ህ/ስራ ማህበር የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የስራ እንቅስቃሴ ሂሳብ ባለሙያ አወዳድሮ ለማስመርመር ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት መወዳደር የምትፈልጉ በአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኤጀንሲ የህብረት ስራ ማህበራትን ሂሳብ በውክልና ለማስመርመር ባወጣው ደንብ ቁጥር 171/2016 እና በመመሪያ ቁጥር 5/2013 ዓ.ም መሰረት፡-

  1. የኢትዮጵያ ሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ወይም እሱ ከሚወክለው አካል ሂሳብ ለመመርመር የሚያስችለውን የሙያ ፈቃድ ያገኘ እና ሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል /የምትችል
  2. በሃገሪቱ ህግ መሰረት የኦዲት ስራ ለመስራት የሚያስችል ወቅታዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው ያላት/
  3. የህብረት ስራ ማህበራት ሂሳብ ምርመራ በተመለከተ ከፈዴራል ህብረት ስራ ኮሚሽን እንዲሁም ከአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን ወይም ከሌሎች ህጋዊ አካላት ስልጠና የወሰደ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ቢሆን ይመረጣል ።
  4. ተወካይ ሂሳብ መርማሪ ወይም ከሂሳብ መርማሪው ቡድን አባላት ውስጥ ቢያንስ አንዱ ከዚህ በፊት ህብረት ስራ ማህበራትን ሂሳብ የመረመረ ቢሆን ቅድሚያ ይሰጠዋል።
  5. የህብረት ስራ ማህበራት ሂሳብ ለመመርመር ብቁ ባለሙያዎችን በስራ ላይ ማሰማራት የሚችል ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚከተለው ማንኛውም ኪሳራና አስቀድሞ ኃላፊነቱነ የሚወስድ፣
  6. እንደ አስፈላጊነቱ አግባብ ባለው ባለስልጣን የሚጠየቁ ሌሎች መረጃዎችን ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
  7. 100% ዝርዘር የኦዲት ምርመራ ማድረግ የሚችል
  8. ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ የውል ማስከበሪያ 10% በሲፒኦ ማስያዝ የሚችል
  9. ህጋዊ የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ TIN NO,VAT እና ማህተም ያለው /ያላት/
  10. 2% ሲፒኦ ማስያዝ የሚችል /የምትችል/

ተወዳዳሪዎች የአጋፔ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/ህ/ስራ ማህበር ቢሮ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በ 50 ብር /ሃምሳ ብር/ በመግዛት ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ በፖስታ በማሸግ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ሰነዱን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እንድታስገቡና ጨረታውም በ11 ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸን ቢገኙም ባይገኙም ታዛቢዎች በተገኙበተ በይፋ ይከፈታል።

ማሳሰቢያ ፡- ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ በሰአቱ ሳይገኙ ቢቀሩ በተገኙት አባላት ይከፈታል። ባለመገኘት ለሚቀርብ ቅሬታ ተቀባይነት የለውም።

አድራሻ፡- ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ፖሊስ ጣቢያ አጠገብ ኢምፔሪያስ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ላይ እንገኛለን።

ለበለጠ መረጃ:- 0906-562222/0906-572222

 

አጋፔ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/ህ/ስራ ማህበር

 

Save Tender