Tender Detail

Tender Details


በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ላሉት ለተለያዩ መንግስት መስሪያ ቤቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


ግስጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ላሉት ለተለያዩ መንግስት መስሪያ ቤቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

እነሱም-

1, የፅህፈት መሳሪዎች፤

2 ቋሚ አላቂ ዕቃዎች እና የፅዳት ዕቃዎች፤

3. የኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር ዕቃዎች፤

4. የደንብ ልብሶችን

ከዚህ በታች የቀረበውን መስፈርት የምታሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

አስፈላጊ መስፈርቶች:-

1. ተጫራቾቹ ከሚጫረቱበት ዕቃ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለውና ዕቃዎቹን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለውና የዘመኑ ግብር የከፈለ፤ VAT ተመዝጋቢነት እና TIN NO. እንዲሁም የምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።

2. የጨረታ ማስከበሪያ ተመላሽ የሚሆን በተ.ቁ 1፣ 2፣ 3 እና 4 (ሁሉም ላይ) ከተወዳደሩ 10,000.00 (አስርሺህ ብር) በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

3. ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) ብር ከፍሎ መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸው ላይ መ/ቤታችን በሰጣቸው የጨረታ ሰነድ ላይ የአንዱ ዋጋ የሚለው ቦታ ላይ ተጨማሪ እሴት ታከስ ያካተተ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላትና የድርጅታቸውን ማህተም፣ ፊርማና ሙሉ አድራሻቸውን በመግለፅ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ በሥራ ሰዓት እስከ ቀን 06/01/2018 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት በአንድ ጥቅል ፖስታ በማሸግ አዳባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

5. ጨረታው የሚከፈተው ተወዳደሪዎች ወይም ህጋዊ ውክልና ያላቸው ሰዎች ባሉበት ይሆናል።

6. ከ100.000.00 (አንድ መቶ ሺህ) በላይ ያሸነፈ ተጫራች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለበት።

7. ጨረታው የሚከፈተው ከዚህ በላይ የተጠቀሱት ቀናቶች አልቆ በቀን 06/01/2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል።

8. የሚቀርቡት ዕቃዎች ጥራት ያላቸውና በተሰጠው ስፔስፊኬሽን መሰረት ተሟልተው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

9. የዕቃው አቅርቦት ቦታ አዳባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ሲሆን ማስጫኛና ማውረጃን ጨምሮ ይሆናል።

10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አመራጭ ከገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11.ለተጨማሪ መረጃ፡- 022-6-63-02-55/09-13-15-09-29/09-15-81-08-37 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

Save Tender