ብርሃነ ወንጌል መጥምቃውያን ቤተ ከርስቲያን ልማት ድርጅት በምስራቅ ወለጋ ዞን ባሉ 3 ወረዳዎች ማለትም ዲጋ ወረዳ ፤ ዋዩ ቱቃ ወረዳ እና ስቡ ስሬ ወረዳዎች ላይ ከታች የተዘረዘሩትን አቅርቦቶች ለማግኘት ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን አቅራቢዎች ማወዳደር ይፈልጋል፡፡
የብርሀን ወንጌል መጥምቃዊያን ቤተክርስቲያን የልማት ድርጅት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-01/2017
በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ እና ከታች በተዘረዘሩ መዳረሻ ቦታዎች ድረስ የተዘረዘሩትን የምግብ ዓይነቶች ማቅረብ የሚችል የጨረታ ሰነዶቻችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡
የመወዳደሪያ መስፈርቶች፡-
- አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ አቅራቢነት ፈቃድ፡-
- የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት (TIN Certificate) ማቅረብ የሚችል፡-
- የዓመቱን ግብር የከፈሉበትን ታከስ ክሊራንስ ማስረጃ፦
- ከዚህ በፊት ተመሳሳይ አቅርቦት ያደረጉበት ልምድ (ካለ)፦
- ሌሎች ሕጋዊ ደጋፊ ማስረጃዎች (ካለ)፡-
|
ተ.ቁ |
የአቅርቦት አይነት |
ብዛት በኪሱ ግራም |
መዳረሻ ቦታ |
|
1 |
1ኛ ደረጃ በቆሎ |
85,350 ኪ.ግ |
ሲቡ ስሬ ወረዳ (ስሬ ከተማ) |
|
2 |
1ኛ ደረጃ በቆሎ |
84,000 ኪ. ግ |
ዋዩ ቱቃ ወረዳ (ጉቴ ከተማ |
|
3 |
1ኛ ደረጃ በቆሎ |
60,000 ኪ. ግ |
ዲጋ ወረዳ መጋዘን ( ጉደቱ አርጆ ከተማ) |
|
4 |
1ኛ ደረጃ በቆሎ |
6,000 ኪ. ግ |
ሲቡ ስሬ ወረዳ (ስሬ ከተማ) |
|
5 |
1ኛ ደረጃ በቆሎ |
8,400 ኪ. ግ |
ዋዩ ቱቃ ወረዳ (ጉቴ ከተማ) |
|
6 |
1ኛ ደረጃ በቆሎ |
6,000 ኪ. ግ |
ዲጋ ወረዳ መጋዘን ( ጉደቱ አርጆ ከተማ) |
|
7 |
የምግብ ዘይት |
2,560.5 ሊትር |
ሲቡ ስሬ ወረዳ (ስሬ ከተማ) |
|
8 |
የምግብ ዘይት |
2,520 ሊትር |
ዋዩ ቱቃ ወረዳ (ጉቴ ከተማ |
|
9 |
የምግብ ዘይት |
1,800 ሊትር |
ዲጋ ወረዳ መጋዘን ( ጉደቱ አርጆ ከተማ) |
|
10 |
ፋፋ የልጆች ምግብ |
9,000 ኪ. ግ |
ሲቡ ስሬ ወረዳ (ስሬ ከተማ) |
|
11 |
ፋፋ የልጆች ምግብ |
9,000 ኪ. ግ |
ዋዩ ቱቃ ወረዳ (ጉቴ ከተማ) |
|
12 |
ፋፋ የልጆች ምግብ |
6.111 ኪ. ግ |
ዲጋ ወረዳ መጋዘን ( ጉደቱ አርጆ ከተማ) |
ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ የባንከ ከአጠቃላይ ዋጋው 2 በመቶ የማያንስ የባንክ ዋስትና ማስያዣ (ሲፒአ) ለእያንዳንዱ ዕቃ የጨረታ ሰነድ በብር 300 (ሶስት መቶ) በመግዛት የመወዳደሪያ ሰነዳችሁን እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ትችላላችሁ፡፡ ጨረታው በማግስቱ በጳጉሜን 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች በተገኙበት ይከፈታል፡፡
አድራሻ፡- ቂርቆስ ከፍለ ከተማ ወረዳ 04 ቄራ አካባቢ ውልና ማስረጃ ያለበት ኤስዲ ሕንፃ ቀጥሎ ያለው ግቢ ውስጥ፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 011-466-184/091-37-07-76/0911-68-31-23 ፖስታ ሳጥን ቁጥር፡ 24064 ኮድ 1000
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዕቃ ለእያንዳንዱ ቦታ ተመሳሳይ ጥራት የጠበቀ መሆን አለበት፡፡
በተጨማሪ የሚያቀርቡት ዋጋ የተ.እ.ታክስ ያካተተ መሆን አለበት። የብርሃነ ወንጌል መጥምቃውያን ቤተክርስቲያን የልማት ድርጅት ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
የብርሀን ወንጌል መጥምቃዊያን ቤተክርስቲያን የልማት ድርጅት
