በአ.ብ.ክ.መ በደቡብ ወሎ ዞን በአልብኮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ንብ/አስ/ቡድን ለ2018 በጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ የተሽከርካሪ ሞዴል LAN-25,1HZ-78,1HZ-78, 1HZ-79 440 ትራክተር፣ ተሽከርካሪዎች የዕቃ መለዋወጫ እና ጎማ በበጀት ዓመቱ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በአ.ብ.ክ.መ በደቡብ ወሎ ዞን በአልብኮ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2017
በአ.ብ.ክ.መ በደቡብ ወሎ ዞን በአልብኮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ንብ/አስ/ቡድን ለ2018 በጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ የተሽከርካሪ ሞዴል LAN-25,1HZ-78,1HZ-78, 1HZ-79 440 ትራክተር፣ ተሽከርካሪዎች የዕቃ መለዋወጫ እና ጎማ በበጀት ዓመቱ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
ስለዚህ ተጫራቾች፡-
- የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው/ያላትና ግብር የከፈለ/ች
- የሚወዳደሩት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ ማስረጃ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል/የምትችል
- በዘርፍ የንግድ ስራ ፈቃድ ያለው/ያላት
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
- ውድድሩ በድምር ውጤት ሲሆን የውለታው ጊዜ እንደ አስፈላጊነቱ በበጀት ዓመቱ ሊሆን ይችላል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋውን በመሙላት ኦሪጅናሉን ኮፒውን በጥንቃቄ በታሸገ ኤንቨሎፕ/ፖስታ ከጨረታ ማስከበሪያው ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን 2% በጥሬ ገንዘብ፣ ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን አልቡኮ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 09 ድረስ በመገኘት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱ በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህንን ማስታወቂያ የያዘው ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀን በአየር ላይ በመቆየት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ40 ተከታታይ ቀን ይቆያል፡፡
- የጨረታ ሰነድ የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአልቡኮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ይከፈታል፡፡
- በወጣው የጨረታ ሰነድ ላይ ጥያቄ ማብራሪያ ወይም ቅሬታ ካለ በህጉና በአዋጁ መሰረት አል/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 19/11 በፅሁፍ ማቅረብ ይቻላል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር 033 215 00 32
በአ.ብ.ክ.መ በደቡብ ወሎ ዞን የአልብኮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
