Tender Detail

Tender Details

  • Company በአብክመ ገንዘብ ቢሮ በሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቁ.4 ሰላድንጋይ
  • Address ሰሜን ሸዋ ዞን ከደ/ብርሃን 72 ኪሎ ሜትር ወደ ደሴ መስመር ከሚወስደው መንገድ ጣርማበር (ዋሻ) ወደ ምዕራብ 22 ኪሎ ሜትር ገባ ብሎ ሰላድንጋይ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116250146
  • Website
  • Deadline09 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityለጽሕፈት መሳሪያ 25,000 /ሃያ አምስት ሺህ/ ብር፣ የጽዳት እቃዎች 5,000 /አምስት ሺህ/፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ፣ ለሚሠሩ ፈርኒቸሮች 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ፣ ለመኪና እቃ አቅርቦት 25,000 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ ፣ ለመኪና ጥገና 10,000 /አስር ሺህ ብር/
  • opening date2025-09-09 00:00:00
  • Categories Furniture And Furnishing , Cleaning And Janitorial Equipment , Vehicle (Garage Service) , Stationery Materials , Electronics Materials , Vehicle Spare Parts

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች የተለያዩ አላቂና ቋሚ የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ አላቂ የጽዳት ዕቃዎች፤ የሚሠሩ የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸሮች የኮንትራት አቅርቦት የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ የኮንትራት አቅርቦት የኮንትራት አቅርቦት የመኪና ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሠራት ይፈልጋል፡፡

በአብክመ ገንዘብ ቢሮ በሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቁ.4 ሰላድንጋይ


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች የተለያዩ አላቂና ቋሚ የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ አላቂ የጽዳት ዕቃዎች፤ የሚሠሩ የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸሮች የኮንትራት አቅርቦት የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ የኮንትራት አቅርቦት የኮንትራት አቅርቦት የመኪና ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣
  2. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 / ሁለት መቶ/ ብር ብቻ በመክፈል ሰነዱን ከግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ማግኘት ይቻላል፣
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለጽሕፈት መሳሪያ 25,000 /ሃያ አምስት ሺህ/ ብር፣ የጽዳት እቃዎች 5,000 /አምስት ሺህ/፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ፣ ለሚሠሩ ፈርኒቸሮች 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ፣ ለመኪና እቃ አቅርቦት 25,000 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ ፣ ለመኪና ጥገና 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ መሂ ማስያዝ አለባቸው፣
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ሁሉም ጨረታዎች ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ማሻሻያ ወይም ማብራሪያ ካላቸው ለእቃና አገልግሎት ግዥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 /አስር/ ቀናት ለግ/ንብ/አስ/ቡድን በጽሑፍ ማቅረብ ይችላሉ።
  7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ድረስ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 0116250146 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. የጨረታ መዝጊያው ቀን እሑድና ቅዳሜ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፤

አድራሻ፡- አማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከደ/ብርሃን 72 ኪሎ ሜትር ወደ ደሴ መስመር ከሚወስደው መንገድ ጣርማበር (ዋሻ) ወደ ምዕራብ 22 ኪሎ ሜትር ገባ ብሎ።

 

በአብክመ ገንዘብ ቢሮ በሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቁ.4 ሰላድንጋይ

 

Save Tender