Tender Detail

Tender Details


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቃ/ቃ/ክ/ከተማ ወረዳ 6 አስተዳደር ጽ/ቤት ከዚህ በታች በዝርዝር የተቀመጡትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቃ/ቃ/ክ/ከተማ ወረዳ 6 አስተዳደር ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 ግዥ መለያ ቁጥር 01/18

 

ሎት-1-የደንብ ልብስ                                                          ሎት-2- አላቂ የቢሮ እቃዎች

ሎት-3- የፅዳት ዕቃዎች                                                       ሎት-4-ልዩ ልዩ ዕቃዎች

ሎት-5- ቋሚ የቢሮ እቃዎች                                                ሎት-6- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

ሎት-7- ቋሚ የቢሮ እቃዎች ጥገና                                        ሎት-8- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና

ሎት-9- የህትመት ሥራ አገልግሎት                                      ሎት-10-የትራንስፖርት አገልግሎት

ሎት-11- የጉልበት ሥራዎች እና የዲኮር አገልግሎት

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች፡-

  1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸው የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin) የተመዘገቡበትን ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው፣
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
  5. በአቅራቢዎች ስም ዝርዝር የተመዘገቡበትን መረጃ ማቅረብ አለባቸው፣
  6. ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በአቃ/ቃ/ክ/ከ/ወረዳ 6 ፋይናንስ ጽ/ቤት በሚል ስም አሠርቶ ከሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
  7. የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመግዛት በአቃ/ቃ/ክ/ከ/ወረዳ 6 ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ 3ኛ ፎቅ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀን በአየር ላይ ቆይቶ በ10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት የጨረታ ሣጥኑ ይታሸጋል፡፡ የጨረታ ሰነዱ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ የገዙትን የጨረታ ሰነድ ሙሉውን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) 2% በአቃ/ቃ/ክ/ከ/ወረዳ 6 ፋይናንስ ጽ/ቤት በሚል ስም አሠርቶ ከሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኮፒ በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒ ብሎ በመለየት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  10. ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ ከ1 ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣ ዝርዝር እስፔስፍኬሽ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ጨረታው የሚከፈተው ከ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች (ሕጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት ሲሆን ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፣
  12. ተጫራቾች በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት የለባቸውም፣
  13. የሚሞላው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፣
  14. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- አቃ/ቃ/ክ/ከተማ ወረዳ 6 አስተዳደር ጽ/ቤት

ሣሪስ - ከሬስ ኢንጂነሪኒንግ ከፍ ብሎ

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቃ/ቃ/ክ/ከተማ ወረዳ 6 አስተዳደር ጽ/ቤት

 

Save Tender