Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ
  • Address አራዳ ክ/ከተማ ፒያሳ በሚገኘው የመንግስት ሰራተኞች የጡረታ ዋስትና ህንፃ ከቸርቸር ጎዳና ወደ እሪ በከንቱ በሚወስደው መንገድ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011118132208
  • Website
  • Deadline03 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር)
  • opening date2025-09-03 00:00:00
  • Categories Vehicle , Transportation Service And Cargo

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚሆን የተለያዩ የቢሮ አገልግሎቶችን በ2018 በጀት አመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ


 

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር አ/አ/ኢ/ቴ/ል/ቢ/ግ/ጨ/ቁ-002/2018

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚሆን የተለያዩ የቢሮ አገልግሎቶችን በ2018 በጀት አመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የአገልግሎት ግዥዎች፡-

ለሎት 1. የመኪና የአገልግሎት ግዥ፣

    1. ደረጃውን የጠበቀ ቱክሰን መኪና ከ2020 ሞዴል በላይ
    2. ደረጃውን የጠበቀ ሀዩንዳይ መኪና ከ2020 ሞዴል በላይ
    3. ደረጃውን የጠበቀ ሀርድ ቶፕ መኪና ከ2020 ሞዴል በላይ

ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች/ ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋበዛሉ።

  1. ተጫራቾች የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ እና የምዝገባ ምስከር ወረቀት ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር በአቅራቢነት መመዝገባቸው የሚገልጽ የምስክር ወረቀት፣ የቫት ተመዝጋቢነታቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም ግብር መክፈላቸውን የሚያሳይ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይገባቸዋል።
  2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ማለትም ከ18/12/2017 ዓ.ም ጀምሮ ከሎት 1.1 እስከ ሎት 1.3 የተጠቀሱትን ጨረታዎች ለተከታታይ 10 ቀናት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ 13ኛ ፎቅ ፋይናንስ ዳሬክቶሬት ክፍል በመገኘት ከሎት 1.1 እስከ ሎት 1.3 ላሉት ብር 300.00 የማይመለስ በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል።
  3. ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ ሰነድ ውስጥ የተገለፀውን ማለትም ከሎት-1.1 እስከ ሎት1.3 ላሉት ለእያንዳንዳቸው ብር 20,000.00 በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንቲ በማቅረብ በኢትዮጵያ ውስጥ ለማቅረብ ከባለስልጣን መ/ቤቱ ፍቃድ የተሰጠው መሆኑን የሚገልፅ ሰነድ እንዲቀርብ ይጠበቃል።
  4. የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ሲፒኦ ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ ያሸነፉበትን ዋጋ 10% ማስያዝ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንታቸውን ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ሙሉ አድራሻ እና የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው ተከታታይ ቀን በመቁጠር ጨረታው በወጣ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮችን 14ተኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ክፍል ይከፈታል።
  7. እያንዳንዱ ተጫራች ሌሎች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም
  8. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ቫትን ጨምረው መሙላት አለባቸው።

ስልክ ቁጥር፡- 011118132208

አድራሻ ፡- አራዳ ክ/ከተማ ፒያሳ በሚገኘው የመንግስት ሰራተኞች የጡረታ ዋስትና ህንፃ ከቸርቸር ጎዳና ወደ እሪ በከንቱ በሚወስደው መንገድ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ 13ኛ ፎቅ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ

 

Save Tender