Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Shipping and Logistics (የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ)
  • Address Ras Mekonen Street, Leghar behind Ethiopian Insurance Corporation H.Q., Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 251115549300
  • Websitehttps://www.eslse.et/
  • Deadline01 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-09-01 00:00:00
  • Categories Metals And Metal Working , Used Items , Vehicle Spare Parts

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ በየተቋማቱ የሚገኙ አገልግለው የተመለሱ የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ለመሸጥ ይፈልጋል።

Ethiopian Shipping and Logistics (የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ)


 

አገልግሎት ሰጥተው የተመለሱ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች የግልፅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር DIS 02/2017

 

ታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓ.ም በቁጥር ገ/ኢ/1/53/68 ከገንዘብ ሚኒስቴር ለድርጅታችን በቀጥታ በፃፈው ደብዳቤ በየተቋማቱ የሚገኙ የቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ ስከራፕ የተደረጉ ተሽከርካሪዎች፤ ማሸነሪዎች እና አገልግሎት ሰጥተው ወደ መጋዘን የተመለሱ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን በኪሎ ግራም ዋጋ ለብረታ ብረት አቅላጭ በውድድር እንዲሸጥ በፈቀደው መሰረት አገልግሎት ሰጥተው ወደ መጋዘን የተመለሱ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን እና የመሳሰሉትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የገንዘብ ሚኒስቴር ለብረት አቅላጭ በኪሎ ግራም የገቢያ መነሻ ዋጋ ብሎ በወሰነው መሰረት በብረታ ብረት አቅላጭነት የተሰማሩትን በገበያ በማወዳደር ለመሸጥ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል። ይሁን እንጂ አገልግለው የተመለሱ የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች በወጣው ጨረታ ገዥ ባለመቅረቡ በድጋሚ ባሉበት ሁኔታ ለመግዛት ፍላጎት ላለው ማንኛውም ተጫራች መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ ፍቃደኛ የሆነ ድርጅት/ግለሰብ በድርጅታችን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቅዳሜ ነሐሴ 17 ቀን 2017ዓ.ም በኋላ ባሉት የሥራ ቀናት ማለትም ከሰኞ ነሐሴ 19 ቀን 2017ዓ.ም ጀምሮ እስከ አርብ ነሐሴ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ/ በመክፈል ለገሃር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ ስድስተኛ ፎቅ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት መምሪያ ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

ጨረታው ሰኞ ነሐሴ 26 ቀን 2017ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልፅ የሚከፈት ሲሆን ሰነድ የገዙ ተጫራቾች በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ 6ኛ ፎቅ በመቅረብ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን የጨረታ ሰነዱን በፖስታ ውስጥ በማሸግ እስከ ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል። ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በራሳቸው ፈቃድ ካልተገኙ ተቋሙ ጨረታውን ከመከፈት አይታገድም፡፡

ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስለ ጨረታው የበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115549257/0951414204 ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል።

 

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ

 

Save Tender