በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ በወረዳ 12 ስር በመጋቢት 28 ቅድ/አ/አ/መካ/ደ/ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ እቃዎች አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ በወረዳ 12 ስር በመጋቢት 28 ቅድ/አ/አ/መካ/ደ/ት/ቤት
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መሰያ ቁጥር፡ መጋቢት 28 ቅድ/ስ/ስ/መካ/ደ/ትቤት/01/2018
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ በወረዳ 12 ስር በመጋቢት 28 ቅድ/አ/አ/መካ/ደ/ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ
ሎት 1 የጽሕፈት መሳሪያ--የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000
ሎት 2 የአይሲቲ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 4,000
ሎት 3 የፅዳት እቃዎች -የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000
ሎት 4 የደንብ ልብስ--የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000
ሎት 5 የስፖርት ትጥቅ— የጨረታ ማስከበሪያ ብር 7.000
ሎት 6 የጥገና ዕቃዎች -የጨረታ ማስከበሪያ ብር 6,000
ሎት 7 ቋሚ ዕቃዎች —የጨረታ ማስከበሪያ ብር 7,000
ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል በዚህም መሰረት-
1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድረ ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ፣ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. ተጫራቾች ለእንያንዳንዱ ሎት የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ (CPO) ከጨረታው ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 /አስር/ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል በመጋቢት 28 ቅድ/አ/አ/መካ/ደ/ትቤት የቢሮ ቁጥር 3 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ኮፒና ኦርጅናሉን በመለየት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 ሰጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል፡፡ የመከፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎት 1፣ ሎት 3፣ ሎት 4፣ ሎት 5፣ ሎት 6 እና ሎት 7 ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለሎት 2 በቀረበው የፍላጎት መግለጫ /Specification/ መሰረት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
7. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
8. የዘገየ ጨረታና በጨረታ መከፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ ጥያቄ
አድራሻ : ሳሪስ በዳማ ሆቴል 58 ታከሲ ማዞሪያ ግንቦት 20 ት/ቤት አጠገብ የመ/ቤቱ ስልከ ቁጥር 0114-191533
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ በወረዳ 12 መጋቢት 28
ቅድ/አ/አ/መካ/ደ/ት/ቤት
