በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የሸገር ከተማ አስተዳደር የኮዬ ፈጬ ከፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተገለጸውን መመሪያ /መረጃዎች በማቅረብ/ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የሸገር ከተማ አስተዳደር የኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የሸገር ከተማ አስተዳደር የኮዬ ፈጬ ከፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለሴከተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ፡-
* የጽህፈት መሳሪያ እና የጽዳት ዕቃዎች ፣
* የመኪና ጎማዎች ፣
* ፈርኒቸር (ቋሚ ዕቃዎች) ፣
* ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች (ቋሚ ዕቃዎች) ፣
* የደንብ ልብሶች አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተገለጸውን መመሪያ /መረጃዎች በማቅረብ/ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
1- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፡፡
2- የአቅራቢዎች ዝርዝር ተርታ የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆኑ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣
3- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15) ተከታታይ የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 1500.00 (አንድ ሺ አምስት መቶ) ብር በኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት በመከፈል ሰነዱን ከኮዬ ፈጬ ከፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ፡፡
4- ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር (ሰነድ) ዋና እና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ/ በፖስታ/ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15) ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ በኮዬ ፈጬ ከፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በተዘጋጀነው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል፡፡
5- ጨረታው በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ (ተዘግቶ) በዚሁ ቀን 4፡ 30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮዬ ፈጬ ከፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል፤ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡
6- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንከ በተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
7- ተጫራቾች ጨረታውን አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል::
8- ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በኋላ በተገለፀላቸው ቀን ቀርበው ውል ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
9- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተገለፀው መሰረት የተጫረተበትን ዕቃ ናሙና /Sample/ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል::
10- ጥራት (Quality) በሌላቸው እቃዎች ላይ (በኢትዮጵያ ደረጃ መዳቢዎች ከተሰጠ መስፈርት (Standard) በታች የሚያቀርብ ተጫራች) መስሪያ ቤቱ የማይደራደርመሆኑን በቅድሚያ እናሳውቃለን፡፡
11- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለው ማለት አይችልም፡፡
12- ጽ/ቤታችን የሚያጫርታቸውን ዕቃዎች ብዛት እንደ አስፈለጊነቱ እስከ (20%) በመጨመር ወይም በመቀነስ መግዛት ይችላል፡፡
13-መወዳደሪያው በጨረታ ሰነዱ በተዘረዘረው መሠረትተሞልቶመቅረብይኖርበታል::
14- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011439-94 93 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ አስተዳደር
የኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
