Tender Detail

Tender Details

  • Company የአርባ ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ
  • Address በአ/ምንጭ ሁለገብ ስታዲየም የክለብ ጽ/ቤቱ ይገኛል። አርባምንጭ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-8-81-36-05
  • Website
  • Deadline06 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security10,000.00 /አስር ሺህ ብር/
  • opening date2025-09-06 00:00:00
  • Categories Hotel Service Provision , Sport Materials And Sportswear

የአ/ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በ2018 ዓ.ም የውድድር ዘመን ተጫዋቾችን በሆቴል ለመመገብ እና የስፖርት ቁሳቁሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊውን በመለየት ለመገልገል እና ለመግዛት ይፈልጋል።

የአርባ ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአ/ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በ2018 ዓ.ም የውድድር ዘመን ተጫዋቾችን በሆቴል ለመመገብ እና የስፖርት ቁሳቁሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊውን በመለየት ለመገልገል እና ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን ማሟላት የምትችሉ ተወዳዳሪዎች እንድትሳተፉ እየጋበዝን፡

  1. በየዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የንግድ ፈቃዱን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ጨረታ 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በባንከ በተመሰከረ ሲፒኦ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. አሸናፊው ድርጅት ለመልካም የሥራ አፈፃፀም የምስከር ወረቀት⁄ ማስረጃ ማቅረብ የሚችልና የጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ ማስያዝ የሚችል፡፡
  4. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ በአ/ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን እንድትግዙ እየገለጽን እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ መግለጫውን በማያሻማ መልኩ እና ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በመሙላት ሁሉም የጨረታ ሰነዶች ኦሪጅናልና ኮፒ በድምሩ 2 ፖስታዎች በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከፊትና ጀርባው ላይ የድርጅቱን ማህተምና የባለቤትነት ፈርማ በማድረግ በእናት ፖስታ ውስጥ ተጨምሮ ለዚህ አገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ቅዳሜና እሁድን ያካተተ ይሆናል፡፡
  5. የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. በጨረታው ያሸነፈ ተወዳዳሪ የባለሙያ አስተያየት ላይ መሠረት በማድረግ ውል ገብቶ ወደ ስራ የሚገባ ይሆናል፤ ሁሉም ተጫራች አድራሻውንና ቦታውን እንዲሁም የስልክ ቁጥር መግለጽ ይኖርበታል፡፡ በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
  7. የእያንዳንዱ ግዥ መጠን በሽያጭ ሠነዱ ላይ በተገለፀው መሠረት ሃያ በመቶ ሊጨምርም ሆነ ሊቀንስ ይችላል፡፡
  8. መ/ቤቱ የዕቃው ጥራት በባለሙያና በስፖርተኞች ሲረጋገጥ ብቻ ውል ተዋውሎ ማስቀጠል የሚቻል ይሆናል፡፡
  9. በጨረታው ማስታወቂያው ላይ ያልተገለጹ ተጨማሪ ማሳሰቢያዎች በጨረታ ሠነዱ ላይ የሚገለጹ ካሉ እንደ ማስታወቂያው የሚያገለግል ስለሆነ ሁሉም ተጫራች ትኩረት ሊሰጥበት ይገባል፡፡
  10. ክለብ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. ጨረታው የሚከፈተው የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን አንስቶ በ16ኛው ቀን ሲሆን በዕለቱ በ9፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ የሚታሸግ ሆኖ በዕለቱ በ9፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የማይገኙ ከሆነ የጽ/ቤቱን ስራ አያስተጓጎልም፡፡ የተጫራቹ ተወካይ የሚቀርብ ከሆነ ስለ ውክልናው ህጋዊነት የሚገልጽ መረጃ ይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  12. የክለብ ጽ/ቤቱ አድራሻ በአ/ምንጭ ሁለገብ ስታዲየም የሚገኝ ሲሆን ለበለጠ መረጃ በ046-8-81-36-05/09-16-87-84-22) ይደውሉ፡፡

 

የአርባ ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ

 

Save Tender