በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የሰበታ አዋስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት እንደኛ ዙር ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙት መ/ቤቶች የደንብ ልብሶች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን፤ የኤሌከትሮኒከስ እና ፈርኒቸሮች የመኪና እና የሞተር ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የሰበታ አዋስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የሰበታ አዋስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት እንደኛ ዙር ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙት መ/ቤቶች የደንብ ልብሶች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን፤ የኤሌከትሮኒከስ እና ፈርኒቸሮች የመኪና እና የሞተር ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡
የተወዳዳሪዎች መስፈርት
1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊና በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ግዴታ የተወጡ ስለመሆኑ የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
3. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ውስጥ የቀረቡትን ግዴታዎች አምነው መቀበል አለባቸው፡፡
5. ማንኛውም ተጫራች በመንግስት ግዥ መሳተፍ እንደሚችል የሚገልጽ ከህጋዊ አካል የተሰጠ የአቅራቢነት የምስከር ወረቀት ማቅረብ አለበት፡፡
6. የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 የስራ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 / አንድ መቶ/ ብር በመክፈል ከሰበታ አዋስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት ይቻላል፡፡
7. የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሰበታ አዋስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ተጫራቾች በተገኙበት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 4፡30 ይከፈታል፡፡
8. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የተወዳደሩበት የዕቃ ብዛት ተባዝቶ 2% በባንከ በተመሰከረ CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ ብቻ መሆን አለባቸው ፡፡
9. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
10. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
11. ተጫራቾች በፈለጉትና ማቅረብ በሚችሉት ዕቃዎች ላይ ብቻ መወዳደር ይችላሉ፡፡ አሸናፊ ተጫራች /ተወዳዳሪ/ የውድድሩ ውጤት ከተነገረበት እስከ 7ኛው ቀን ቀርቦ ውል ካልፈረመ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ይወረስበታል፡፡
12. ያሰቀመጥነውን ብዛት እንደ አስፈላጊነቱ መጨመር እና መቀነስም ይቻላል፡፡
13. ተጫራቾች በጨረታ ተወዳድረው ያሸነፉበትን ዕቃዎችን ሰበታ አዋስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤ ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት ያቀርባሉ፡፡
14. ተጫራቾች በጨረታው ላይ ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያግድም፡፡
15. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠ ነው፡፡
የሰበታ አዋስ ወረዳ 7ንዘብ ጽ/ቤት
