Tender Detail

Tender Details

  • Company ሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላ/የተ/መ/የህብረት ሥራ ማህበር
  • Address ሜክሲኮ ,ሠንጋተራ የነጋዴዎች ሕንፃ 23ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115571399
  • Websitehttps://shegersacco.com/
  • Deadline30 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security2%
  • opening date2025-09-01 00:00:00
  • Categories Accounting & Auditing , Finance

የሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ሀላ/የተ/መ/የህብረት ስራ ማህበር የ2017 በጀት ዓመትን የማህበሩን ሂሳብ በውጭ ኦዲተሮች ለማስመርመር በኢትዮጵያ አካውንቲንግና ኦዲት ቦርድ /AABE/ እውቅና የተሰጣቸውን የኦዲት ተቋማትን/ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዲዴሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላ/የተ/መ/የህብረት ሥራ ማህበር


 

የውጭ ኦዲተር ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ሀላ/የተ/መ/የህብረት ስራ ማህበር በአዋጅ ቁጥር 985/2009 መሰረት መጋቢት 04/2013 በመቋቋም ባለፉት ዓመታት ለአባላቱ የቁጠባ እና የብድር አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል። በመሆኑም የ2017 በጀት ዓመትን የማህበሩን ሂሳብ በውጭ ኦዲተሮች ለማስመርመር በኢትዮጵያ አካውንቲንግና ኦዲት ቦርድ /AABE/ እውቅና የተሰጣቸውን የኦዲት ተቋማትን/ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዲዴሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች / የኦዲት ድርጅቶች እንድትሳተፋ ተጋብዛችኋል።

ፍላጐት ያላችሁ የኦዲት ድርጅቶች-

  1. ቴክኒካል መነሻ ሀሳብ (Technical proposal)
  2. የፋይናንስ መነሻ ሀሳብ (Financial proposal)
  3. በዘመኑ የታደሰ አግባብ ያለው ህጋዊ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ማስረጃ፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት እንዲሁም የግብር ከፋይነት ሰርቲፍኬት ማቅረብ የሚችል መሆን አለባቸው።
    • የጨረታ ሂደቱ የማህበሩን የግዥ ሃደት የተከተለና በሀገሪቱ የግዥ ህግ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል።
  4. በኢትዮጵያ አካውንቲንግና ኦዲት ቦርድ /AABE/ እውቅና ሰርትፍኬት መቅረብ አለበት።  
  5. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል ሜክሲኮ ሰንጋ ተራ ነጋዴዎች አ/ማ ህንፃ 23 ፎቅ ዘወትር በቢሮ የስራ ሰዓት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ ዋጋውን 2 በመቶ በሲፒኦ /በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ/ ከፋይናንስ ፖስታ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  7. ተጫራቾች ቴክኒካል መነሻ ሀሳብ (Technical proposal) የሚሆናቸውን ዝርዝር ቢጋር (TOR) የያዘ ሰነዴ በማህበሩ የፋይናንስ እና ግዥ ክፍል መውሰድ ይጠበቅባቸዋል።
  8.  ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የስራ ቀናት የሚቆይ /ከሰኞ እስከ አርብ ከጧቱ 2፡30 እስከ 11፡30 እና ቅዳሜ ጧት ከ2፡30 እስከ 6፡30/ ሆኖ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል መነሻ ሀሳብ ሰነዳቸውን ካስገቡ በኋላ በእለቱ 10ኛው ቀን ከሰአት በኋላ 11፡30 ላይ ተዘግቶ በማግስቱ ማለትም በ11ኛው የስራ ቀን ላይ ጧት በ4፡00 ሰዓት በማህበሩ ዋና ቢሮ የሚከፈት ይሆናል።
  9.  የጨረታው መክፈቻ 11ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት በማህበሩዋና ቢሮ የሚከፈት ይሆናል።
  10. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. ስለ ጨረታው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ከፈለጉ ቀጥሎ ባለው የስልክ ቁጥር ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

ስልክ 0115571399 ወይም 0948051115 ወይም

0911997050

 

ሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ሀላ/የተ/መ/የህብረት ስራ ማህበር አዲስ አበባ

 

Save Tender