Tender Detail

Tender Details


በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የአብቹና ኘኣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት አንደኛ ዙር ግዥ በወረዳው ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ህትመቶች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የመኪና፣ የሞተር መለዋወጫ እቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ ውስጥ ፈርኒቸሮች፣ ኤሌከትሮኒክስ እቃዎች (ኮምፒውተሮች የመሳሰሉትን) ፣ ጄኔሬተሮች፣ የመኪና፣ የሞተር ጎማዎች፣ የግንባታ ዕቃዎች፣ የውሃ እቃዎች፣ የስልጠና ዕቃዎች እና የሰራተኞች የደንብ ልብስ በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የአብቹና ፕአ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


                                                         የጨረታ ማስታወቂያ


 

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የአብቹና ኘኣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት አንደኛ ዙር ግዥ በወረዳው ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ህትመቶች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የመኪና፣ የሞተር መለዋወጫ እቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ ውስጥ ፈርኒቸሮች፣ ኤሌከትሮኒክስ እቃዎች (ኮምፒውተሮች የመሳሰሉትን) ፣ ጄኔሬተሮች፣ የመኪና፣ የሞተር ጎማዎች፣ የግንባታ ዕቃዎች፣ የውሃ እቃዎች፣ የስልጠና ዕቃዎች እና የሰራተኞች የደንብ ልብስ በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች፡-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

  2. በገንዘብ ሚ/ር የዕቃ አቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀትና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያለው፡፡

  4. ተጫራቾች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር የያዘውን የመጫረቻ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የዕቃዎቹን ስፔስፊኬሽን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት በአብቹና ኘኣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመምጣት ከቢሮ ቁጥር 04 መግዛት ይችላሉ፡፡

  5. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በተዘጋጀው ሰነድ ሞልተው በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒውን በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 4 መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

  6. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አሥር ሺህ) በባንክ የተመሰከረ CPO ማቅረብ የሚችል።

  7. ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15ኛው የሥራ ቀን ሆኖ በዚሁ ቀን በ6፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ7፡40 ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በቀጣዩ የሥራ ቀን በ7፡40 ሰዓት በወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ይከፈታል።

  8. አሸናፊው ድርጅት ዕቃውን አብቹና ፕአ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በማምጣት ማስገባት አለበት።

  9. የተጠየቁትን ዕቃዎች ሠርዘው ወይም ደልዘው መጻፍ ክልክል ነው።

  10. የዕቃውን ኮድ ወይም አይነት ለመቀየር ከፈለጉ ከታች ማሳሰቢያ ብለው በመፃፍ ይፈርሙበት።

  11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

  12. የተጠየቁት ዕቃዊች በሙሉ ደረጃቸውን የጠበቁና ኦርጅናል መሆን አለባቸው።

       ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0913299765 / 0116210035 ደውለው ይጠይቁ።

                               ኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የአብቹና ኘኣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


 


 

Save Tender