የትግል ለነፃነት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ትግል ለነፃነት ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ትለ 001/2018 ዓ.ም
የትግል ለነፃነት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
1ኛ/ የደንብ ልብስና የወንድና የሴት ጫማዎች
2ኛ/ አላቂ የጽዳት ዕቃዎች
3ኛ/ የትምህርት የጽሕፈት መሣሪያዎች
4ኛ/ የቢሮ አላቂ ዕቃዎች
5ኛ/ የስፖርት ትጥቆች እና የስፖርት ዕቃዎች
6ኛ/ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች
7ኛ/ የሕንፃ መሣሪያዎች
8ኛ/ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
ተጫራቾች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉና የቫት የምዝገባ ወረቀት አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ያሸነፉበትን ዕቃ ግዥ መ/ቤት ድረስ በራሳቸው ወጪ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የእንዱን ዋጋ ሲያቀርቡ ከነቫቱ ደምረው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት አለባቸው። ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ በመ/ቤቱ ሰነድ ላይ ብቻ መሆን አለበት፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ማስገቢያ ቀን ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ይሆናል።
- ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት ዕቃዎችን ማስረከብ ያለበት ማሸነፉ ከተነገረው በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ማስገቢያ ት/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይሆናል፡፡
- የጨረታውን ሰነድ ከላይ በተራ ቁጥር 4 የተጠቀሰውን ገንዘብ በመክፈል በት/ቤቱ ፋይ/ግ/ን/አስ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 መውሰድ ይቻላል፡፡
- ጨረታው በወጣ በአስራ አንደኛው ቀን 4፡15 /አራት ሰዓት ከሩብ/ ታሽጎ 4፡30 /አራት ሰዓት ተኩል/ በት/ቤቱ አዳራሽ ሕጋዊ ተጫራቾቻቸው ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለጨረታ ማስከበሪያ ብር ከታች የተገለጸውን በባንክ የተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነድ ጋር እያይዞ ማቅረብ አለበት፡፡ የደንብ ልብስና የወንድና የሴት ጫማዎች ብር 3000 /ሶስት ሺህ/፣ የአላቂ የጽዳት ዕቃዎች ብር 5000 /አምስት ሺህ ብር/፤ የትምህርት እና የጽህፈት መሣሪያዎች ብር 5500 /አምስት ሺህ አምስት መቶ ብር/፣ የቢሮ አላቂ ዕቃዎች ብር 5000 /አምስት ሺህ/ የስፖርት ትጥቆች እና የስፖርት ዕቃዎች ብር 4000 /አራት ሺህ/ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ብር 3500 /ሶስት ሺህ አምስት መቶ/፤ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ብር 4500 /አራት ሺህ አምስት መቶ/፤ የሕንፃ መሣሪያዎች ብር 3500 /ሶስት ሺህ አምስት መቶ/ እንዲሁም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ብር 4000 /አራት ሺህ ብር/፣
አድራሻ፡- ትግል ለነፃነት ቅድመ አንደኛና አንደኛ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በየካ ክፍለ ከተማ በቀድሞ ቀበሌ 01/02 በአዲሱ ወረዳ 01 ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ሳይደርስ 800 ሜ ሲቀረው 41 ቁጥር አውቶብስ መሄጃ መስመር
ማሳሰቢያ፡- ለጥራት 80% ለዋጋ 20% ስለሆነ ለጥራት ከምንም በላይ ቅድሚያ እንሰጣለን፡፡
የአንዱን ዕቃ ዋጋ ስታቀርቡ ከነቫቱ ማቅረብ አለባችሁ፡፡
ቫት ሳያካትት ዋጋ ያቀረበ ድርጅት ጨረታው ውድቅ ይሆንበታል፡፡
ማንኛውንም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ሲያስገባ ሳምፕል ማቅረብ አለበት፡፡
ማንኛውም ተጫራች መረጃ መጠየቅ ሲፈልግ በሥራ ቀናት ጠዋት 2፡30-11፡30 ባለው ጊዜ ደውሎ መረጃ መጠየቅ ይችላል። ቅዳሜና እሁድ የእረፍት ቀናት ስለሆነ መ/ቤቱ ዝግ ነው፡፡
ስልክ 0111541611/0118120047
ትግል ለነፃነት ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
