በኢፌዴሪ መንግሥት ሰራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የሰሜን ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት ለሪጅኑ እና በስሩ ለሚገኙ ቅርንጫፎች ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ልዩ ልዩ ዕቃዎችን ጽ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ከሚችሉ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በኢፌዴሪ መንግሥት ሰራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የሰሜን ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት ለሪጅኑ እና በስሩ ለሚገኙ ቅርንጫፎች ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ልዩ ልዩ ዕቃዎችን ጽ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ከሚችሉ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የሚገዙ ዕቃዎች ዝርዝር
- የጽህፈት መሳሪያዎች
- የፅዳት ዕቃዎች
- የደንብ ልብስ
- የመኪና ዕቃዎች
- ሌሎች አላቂ ዕቃዎችን
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ። ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ደሴ ከተማ፣ ከመናፈሻ ክፍለ ከተማ ጽ/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው በመንግስት ሰራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የሰሜን ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 13 በመምጣት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ የሚገኘውን የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ በመሙላት ኮፒና ኦርጅናል ለየብቻ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ እስከ 15ኛው ቀን 11:00 ሰዓት ድረስ ፖስታውን ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በ16ኛው ቀን ጠዋት 2፡30 ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 3፡00 ላይ የሚከፈት ሲሆን 16ኛው ቀን የበዓል ወይም የዕረፍት ቀን ከሆነ ጨረታው በተመሳሳይ ሰዓት በቀጣዩ ቀን ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ ደረሰኝ በማስቆረጥ ከኦርጅናል የዋጋ ማቅረቢያ ፖስታ ውስጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- አስተዳደሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የሰሜን ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት
