Tender Detail

Tender Details

  • Company Sidama Region Agriculture Research Institute (የሲዳማ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት)
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0911738584
  • Website
  • Deadline02 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Securityለሎት 1. 15,000.00 (አሥራ አምስት ሺህ ብር) ለሎት 2. 60,000.00 (ስልሳ ሺህ ብር)
  • opening date2025-09-02 00:00:00
  • Categories Construction and Water Works , Building Construction , Construction Works

የሲዳማ ክልል የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በ2017 በጀት ዓመት በዓለም ባንክ ድጋፍ በኤፍ.ኤስ.አር.ፒ ፕሮግራም በሁለት ሎት ማለትም 1) በአበራ ገለዴ ቀበሌ ሊያሰራ ላቀደው የበጎች በረት፣ የላሞች በረት እድሳት እና የውሃ ገንዳ ሥራ እንዲሁም፣ 2 በሎቄ ንዑስ የምርምር ጣቢያ እና የአጥር ሥራ፣ የአሳ ገንዳ እድሳት እና የጥበቃ ቤት ለማሠራት ህጋዊ ተጫራቾችን በአከባቢ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

Sidama Region Agriculture Research Institute (የሲዳማ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የሲዳማ ክልል የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በ2017 በጀት ዓመት በዓለም ባንክ ድጋፍ በኤፍ.ኤስ.አር.ፒ ፕሮግራም በሁለት ሎት ማለትም 1) በአበራ ገለዴ ቀበሌ ሊያሰራ ላቀደው የበጎች በረት፣ የላሞች በረት እድሳት እና የውሃ ገንዳ ሥራ እንዲሁም፣ 2 በሎቄ ንዑስ የምርምር ጣቢያ እና የአጥር ሥራ፣ የአሳ ገንዳ እድሳት እና የጥበቃ ቤት ለማሠራት ህጋዊ ተጫራቾችን በአከባቢ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

  1. ደረጃቸው- GC-6/BC-6 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የሥራ ተቋራጮች 2017 ዓ.ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No.) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን ወይም ከሲዳማ ክልል ኮንስትራከሽን ባለስልጣን የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ።
  2. አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎች፣ የሥራ መሣሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶችን በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መሥራትና ማጠናቀቅ አለባቸው፡፡
  3. በሲዳማ ክልል ውስጥ ሶስት (3) እና ከዚያ በላይ ፕሮጀክቶችን ውል ገብተው ግንባታ እያከናወኑ ያሉ እና ያላስረከቡ ስራ ተቋራጮች ይህን የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፡፡
  4. በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሠርቶ ለማስረከብ ከአሠሪ እና ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በስራ ወቅት ከአሠሪ መስሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መስሪያ ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሥራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፡፡
  5. የሥራ ተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት (ቴክኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦሪጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፤ ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች ከአንድ ሎት በላይ መግዛት እና መወዳደር አይችልም፡፡
  7. የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) ለሎት 1. 15,000.00 (አሥራ አምስት ሺህ ብር) ለሎት 2. 60,000.00 (ስልሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና /BANK GAURANTEE/ ወይም የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  8. የሥራ ተቋራጮች በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ሕጋዊ ፈቃዳቸውን እና ተ.ዕታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፊኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 (አሥራ አምስት) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በሲዳማ ክልል የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ግዥ ፋይናንስ ንብ/አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  9. የሥራ ተቋራጮች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታውን ሳይት በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
  10. የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (bid bond/security)፣ ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ቅጂ (ኮፒ) እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ቅጂ (ኮፒ) ሰነዶችን በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፓስታ ውስጥ በማድረግ በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ግዥ/ፋይናንስ ንብ/ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡
  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቦታ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፣ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን ከመከፈት አያግደውም።
  12. አሠሪው መሥሪያ ቤት የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
  13. አሸናፊው ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሠረት ለቅድመ ክፍያ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  14. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡

 

በሲዳማ ክልል የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት

 

Save Tender