Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115174918
  • Websitehttps://corporate.ethiopianairlines.com/
  • Deadline19 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security100,000.00
  • opening date2025-09-19 00:00:00
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ-በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተርሚናል ሁለት (2) ውስጥ የሚገኙ ከፍት ቦታዎችን ከዚህ በታች ለተጠቀሱ አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)


የቦታ ኪራደ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር: -SSNT-T545

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ-በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተርሚናል ሁለት (2) ውስጥ የሚገኙ ከፍት ቦታዎችን ከዚህ በታች ለተጠቀሱ አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

  • ለባንከ እና ለውጭ ምንዛሬ አገልግሎት የሚውሉ ሁለት (2) ቦታዎች: ተርሚናል 2 መዳረሻ(Arrival
  • ለኤትኤም/ATM አገልግሎት የሚውል ሁለት (2) ቦታዎች: ተርሚናል 2 መዳረሻ (Arrival) በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-

1. በባንክ አገልግሎት ስራ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንከ ህጋዊ ፈቃድ እና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ያለው፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥርያለው እና በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ጨረታ መከፈቻው እለት ድረስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራች በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277( -99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥርSSNT-T545 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ (Deposit Slip) ቅጂውን (scan copy) ፣ የጨረታ ቁጥር፣ የድርጅቱ ስም እና ስልክ ቁጥር ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላከ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡

3. በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንከ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ከኢንሹራንስ እና ቅደመ ሁኔታ ያለው ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

4. ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋናውን እና ቅጂውን ቴክኒካል ሰነድ፣ ዋናውን እና ቅጂውን ፋይናንሻል ሰነድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል እስከ መስከረም 9 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 9:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን 9፡30 ሰዓት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ለተጨማሪ ማብራሪያ:

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ከፍል

በስልክ ቁጥር፡ +251-115-17-89-18

ኢ-ሜይል: ESAYASTS@ethiopianairlines.com

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

Save Tender