Tender Detail

Tender Details


የኢትዮጵያ ቃለህይወት ቤተከርስቲያን ኩሪፍቱ ማዕከል ከዚህ በታች የተመለከቱትን አገልግሎታቸውን የጨረሱ የተለያዩ ማሽኖች የኤሌክትሪክ መሣሪያዎች እንደዚሁም አንድ ጆነዲር ሎደር በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የኢትዮጵያ ቃለህይወት ቤተክርስቲያን ኩሪፍቱ ማዕከል


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኢትዮጵያ ቃለህይወት ቤተከርስቲያን ኩሪፍቱ ማዕከል ከዚህ በታች የተመለከቱትን አገልግሎታቸውን የጨረሱ የተለያዩ ማሽኖች የኤሌክትሪክ መሣሪያዎች እንደዚሁም አንድ ጆነዲር ሎደር በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

  1. አንድ Jhon Deer 310c loader machine
  2. የተለያዩ አሮጌ የኤሌክትሮኒክስ ኮምፒውተር ዕቃዎች
  3. የተለያዩ የብረታ ብረትና በኪሎ የሚሸጡ ቁሳቁሶች
  4. የተለያዩ ማሽኖች ጄኔሬተሮች
  5. የተለያዩ የሴቶች የፀጉር መሥሪያ ዕቃዎች
  6. የተለያዩ ያገለገሉ ጎማዎች እና ባትሪዎች

ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአሥር ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ቢሾፍቱ በሚገኘው የኢትዮጵያ ቃለህይወት ቤተከርስቲያን ኩሪፍቱ ማዕከል በሥራ ሰዓት በመቅረብ የማይመለስ የጨረታ ሰነድ ዋጋ ብር 300.00 ከፍለው መግዛት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሠነድ ማቅረቢያው የመጨረሻ ሰዓት በአሥረኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡ ጨረታው በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት በማዕከሉ ጽ/ቤት ቅጥርግቢ ተጫረቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ:-

  1. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው ከሚከፈትበት አንድ ሰዓት በፊት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች ለሰጡት ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 20% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታው በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ለጨረታ ዋስትና የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎቹ ወዲያው ተመላሽ ይደረጋል፡፡
  3. አሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊነቱ ከተረጋገጠበት ዕለት ጀምሮ በስምንት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ክፍያውን አጠናቆ ንብረቱን ካልተረከበ ያስያዘው ገንዘብ ለማዕከሉ ገቢ ሆኖ አሸናፊነቱ ይሠረዛል፡፡
  4. ማዕከሉ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0912113764 ወይም 0114337169

 

የኢትዮጵያ ቃለህይወት ቤተክርስቲያን ኩሪፍቱ ማዕከል

 

Save Tender