Tender Detail

Tender Details


በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የኮዬ ፈጬ ክ/ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በ2018 የበጀት አመት የተለያዩ ቋሚ፣ አላቂ፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ እና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የኮዬ ፈጬ ክ/ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የኮዬ ፈጬ ክ/ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በ2018 የበጀት አመት የተለያዩ ቋሚ፣ አላቂ፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ እና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ድርጅቶች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

1. ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

2. ተጫራቾች ከ100,000ብር ለሆነ ግዥ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

3. በገንዘብና ትብብር ልማት ሚኒስቴር ወይም በሌላም በሚመለከታቸው ፈቃድ ሰጪ አካላት በአቅራቢነት የተመዘገቡና የምስከር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች ብቻ መካፈል ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት በማይመለስ 100 ብርመግዛት ይችላሉ፡፡

5. ፍ/ቤቱ ካቀረበው መስፈርት /standard/በታች ማቅረብ አይቻልም፡፡

6. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም፡፡

7. ፍ/ቤቱ የሚያጫርታቸውን ዕቃዎች ብዛት እንደ አስፈላጊነታቸው (25%) በመጨመርወይም በመቀነስ ማዘዝ ይችላል፡፡

8. ጨረታው የሚቆየው ለተከታታይ 15 ቀናት ይሆናል፡፡ በ15ኛው ቀን 11፡30 ተዘግቶ በነጋታው በ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡

9. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ተካፋይ ለመሆን ተመላሽ የሚሆን ባቀረበው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 1% የጨረተ ማስከበሪያ /CPO/ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡

10. ፍ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. ፍ/ቤቱ የሚያጫርታቸውን ዕቃዎች ብዛት ለተከታታይ 6 ወራት ውል ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ይዋዋላል፡፡

12. የሚገዙ ዕቃዎች በተሠጠው እስፔስፊኬሽን መሠረት ተሞልተው ካልቀረቡና ማንኛውም ዓይነት ስህተት ቢፈፀም ሃላፊነቱ የአቅራቢው ድርጅት ነው፡፡

አድራሻ፦ ቱሱ ዲምቱ አደባባይ ዩንሳ የሚወስደዉ መንገድ አሴክስ ተብሎ የሚጠራ አካባቢ የሚገኝ የፍርድ ቤቱ ፎቅ 5 ቁጥር የፋይናንስ ክፍል ያገኙናል፡፡ ስተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር-09-24-11-38-72

በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የኮዬ ፈጬ ክ/ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት

Save Tender