በኦሮሚያ ከልላዊ መንግስት መስተዳድር የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ለ2018 ለሥራ የሚገለገልበትን Lot.1. የደንብ ልብስ ሱፍ ሙሉ ልብስ/ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ከልላዊ መንግስት መስተዳድር የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ለ2018 ለሥራ የሚገለገልበትን Lot.1. የደንብ ልብስ ሱፍ ሙሉ ልብስ/ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
- ህጋዊ እና የታደሰ የ2017 ንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (VAT) ያላቸው።
- በገንዘብና ኢኮኖሚልማት ሚንስቴር ወይም በሌላም በሚመለከታቸው ፍቃድ ሰጪ አካላት በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የምስከር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች ብቻ መካፈል ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድመቶ) ብር በመክፈል በመ/ቤቱ ቀርቦ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ለጨረታው ማስከበሪያ ጠቅላላ ካቀረቡት የዕቃ ዋጋ ብር 1% በተረጋገጠ ባንክ (CPO) በድርጅቱ ሰም አሰርቶ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የሚሜረቱበትን የእቃውን ስቴሲፊኬሽን ከድርጅቱ በቀረበው መሠረት በግልፅ በመፃፍና ዕቃው ላይም በግልጽ መታየት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫት ያጠቃለለና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎችን አሟልተው በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ የቢሾፍቱ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ቀርቦ ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ በ10 ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ማስገባት እና ተዘግቶ በዛው ቀን 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ በእለቱ በአል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትከክል ጽፈው መፈረም አለባቸው።
- ድርጅቱ ከሰጠው ስፔስፊኬሽን ውጪ ማስተካከያ ማድረግ እና መሰረዝ (Material Devation) አይቻልም፡፡
- ተጫራቾቸ በድርጅቱ በዋጋ ማቅረቢያ የድርጅቱ ኦርጅናል ማህተም (የቢሾፍቱ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት የሚል ማህተም) ባረፈበት ላይ ብቻ የዕቃ ዋጋዎችን ሞልቶ ማቅረብ አለበት፡፡ ከድርጅቱ ዋጋ ማቅረቢያ ውጪ የሚመጡ ሰነዶች ዋጋ የላቸውም።
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ድርጅታችን ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክተር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-437-1683 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡
የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት
