በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት፣ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን የፈዲስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ለወረዳው የመንግስት መ/ቤቶችና ለቀበሌ መስሪያ ቤቶች የጽህፈትና አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የጽዳት፣ የኤሌክትሮኒክስ፣ ቋሚ እቃ፣ የሞተርና የመኪና መለዋወጫ እና ለግንባታ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የፈዲስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ኮድ፡- 01/2018
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት፣ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን የፈዲስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ለወረዳው የመንግስት መ/ቤቶችና ለቀበሌ መስሪያ ቤቶች የጽህፈትና አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የጽዳት፣ የኤሌክትሮኒክስ፣ ቋሚ እቃ፣ የሞተርና የመኪና መለዋወጫ እና ለግንባታ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህም የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል። ዕቃዎችን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችልና ከዚህ በላይ ለተጠቀሱት የእቃ አይነት ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ለ2018 ዓ.ም የንግድ ፈቃዳቸውን ያደሱና የ2017 ዓ.ም ግብር የከፈሉ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምዝገባ ሰርተፊኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፤
- በገንዘብ ቢሮ በእቃ አቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) ብቻ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ለያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከፈዲስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የዕቃ አይነትና ጥራት ከጨረታው ሰነድ ጋር በተያያዘው ሰንጠረዥ መሰረት መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊዎች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በጨረታው ውል ላይ በተጠቀሱት ቀናት ውስጥ በራሳቸው ወጪ እስከ ወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በገንዘብ ጽ/ቤት ይከፈታል። ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09-21-84-30-77
የፈዲስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
