Tender Detail

Tender Details

  • Company የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ
  • Address ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል : ኢትዮጵያ, Phone: 0473312267
  • Website
  • Deadline05 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security10,000.00
  • opening date2025-09-05 00:00:00
  • Categories Office Supplies And Services , Stationery Materials , Electronics Materials

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የጽሕፈት መሳሪያ እና የቢሮ ጽዳትና ትናንሽ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ


ውሃ/ዕቃ/ግ/ጨ/ቁ-001/2018

የጽሕፈት መሳሪያ ዕቃ ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የጽሕፈት መሳሪያ እና የቢሮ ጽዳትና ትናንሽ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ስመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

  • በጽሕፈት መሳሪያ ዕቃ አቅራቢነት ዘርፍ የተሰማሩ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
  •  በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባና የአቅራቢነት ሰርተፊኬት፣ የቲን (TIN) እና የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች የጨረታ ዶክሜንት ሊገዙ ሲመጡ ኦርጅናሉን እና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ አቅርበው እንዲመሳከር የማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፡
  •  ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር / በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝ/ክል/መ/ውሃ/ማዕ/ኢነ⁄ ቢሮ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ በተከፈተው አካውንት ቁጥር 1000454343507 ገቢ በማድረግ ዘወትር በስራ ሰዓት ለተከታታይ 15 ቀናት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  •  ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.አ/C.P.O/ ወይንም በሁኔታዎች ላይ ያልተገደበ ቢድ ቦንድ /unconditional Bid Bond/ለ90 ቀናት የሚቆይ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝ/ክል/መ/ውሃ/ማዕ⁄ኢነ/ቢሮ ስም በማሰራት ከጨረታው ሰነድ ጋር በማዘጋጀት አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማዘጋጀት አንድ(ı) ኦርጅናልና ሁለት(2) ኮፒ በተለያዬ ፖስታ ታሽጎ ፖስታው ላይ ኦርጅናልና ኮፒ የሚል ጽሑፍ ተለይተው መቅረብ አለበት፡፡
  • ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በእያንዳንዱ የጽሕፈት መሳሪያ፣ የጽዳትና ትናንሽ ኤሌክትሮንከስ ዓይነት በገዙት ኦሪጅናል ሰነድ ላይ ባለው ሰንጠረዥ ከነቫት _ በመጻፍ _ በሰም /በሙጫ/ በታሸገ ኤንቨሎፕ _ በማዘጋጀት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝ/ክል/መ/ውሃ/ማዕ⁄ኢነ⁄ ቢሮ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  • የጨረታው ሳጥን በ16ኛው ቀን ከሰዓት 8፡oo ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከሰዓት 8:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝ/ክል/መ/ውሃ/ማዕ/ኢነ⁄ ቢሮ ይከፈታል፡፡
  • የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ _ ከላይ በተገለጸው መሰረት ይሆናል፡፡ በመክፈቻው ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች ያለመገኘት የጨረታ መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም::
  • አሸናፊ ተጫራች የጽሕፈት መሳሪያ፣ የጽዳትና ትናንሽ ኤሌከትሮንክስ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ _ ህዝ/ክል/መ/ውሃ⁄ማዕ⁄ኢነ⁄ ቢሮ ድረስ በማምጣትና ዕቃውን በማስፈተሽና የማስረከብ ግዴታ አለበት ::
  • የዕቃ ናሙና ላይ የድርጅቱን ክብ ማህተም በመምታት ከጨረታ ዶክሜንት ጋር ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታ ይሰረዛል፡፡
  • ቢሮ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስተጨማሪ መረጃ፡- 0473312267/1819/2005 ደውለው ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የውኃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ

Save Tender