በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የከለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ቡድን በመደበኛ በጀት ለከለላ ወረዳ ሴመቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የቀላል መኪና ጎማ፣ ሎት 2 ዓመታዊ የመኪና ስፔር ፓርት እና ሎት 3 ፋስት ሙቪንግ የመኪና ስፔር ፓርት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የከለላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የከለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ቡድን በመደበኛ በጀት ለከለላ ወረዳ ሴመቤቶች አገልግሎት የሚውል
ሎት 1 የቀላል መኪና ጎማ፣ ሎት 2 ዓመታዊ የመኪና ስፔር ፓርት እና ሎት 3 ፋስት ሙቪንግ የመኪና ስፔር ፓርት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
- የግዥ መጠን ብር ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ሎት ለየብቻ ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ/ ብር በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 (ደረሰኝ) ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊነታቸው ከታወቀ የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ በከለላ ወረዳ ዓቃቢ ህግ ጽ/ቤት ውል በመግባት በተቀመጠው ዝርዝር መግለጫ መሰረት ኦርጅናል እቃ ማቅረብ አለባቸው።
- አሸናፊው ድርጅት በውላቸው መሰረት የመኪና ጎማውን ከለላ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች ድረስ ማስጫኛና ማውረጃን ጨምሮ በማጓጓዝ ማቅረብ እንዳለባቸው እና የመኪና ስፔሩን እስከ ሰኔ 30/2018 ዓ.ም ከአሸናፊው ድርጅት የሚወሰድ መሆኑን መታወቅ አለበት።
- የጨረታ ሰነዱን ከከለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02 የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ/ የኢትዮጵያ ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- የውድድሩ ሁኔታ በጠቅላላ ድምር በሎት ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0334510464 በመደወል
- ማንኛውም ተጫራች በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ዋጋ በመሙላት የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ከለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን 3፡00 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 በ3፡30 ይከፈታል። ሆኖም ግን ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙም የጨረታውን መከፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ ለሚተላለፍ ውሳኔዎች ተገዢ ይሆናሉ።
- የጨረታው መክፈቻ ጊዜ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- መ/ቤቱ የእቃውን 20% የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ
ወሎ ዞን የከለላ ወረዳ ገ/ጽ/ቤ
