በሻሻመኔ ከተማ አስተዳደር መልካ ኦዳ ሆስፒታል 2018 በጀት የተለያዩ ዕቃዎችን እና የኦክስጅን ሲሊንደር ማስሞላትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የመልካ ኦዳ አጠቃላይ ሆስፒታል
የጨረታ ማስታወቂያ
በሻሻመኔ ከተማ አስተዳደር መልካ ኦዳ ሆስፒታል 2018 በጀት የተለያዩ ዕቃዎችን እና የኦክስጅን ሲሊንደር ማስሞላትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- የጽሕፈት መሣሪያዎች
- የፅዳት ዕቃዎች
- የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- ለጤና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ሕትመቶች
- ለሰው ጤና የሚውል የኦክስጅን ሲሊንደር መሙላት
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን መልካ ኦዳ አጠቃላይ ሆስፒታል በመቅረብ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1000 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ በመግዛት በነጠላ ወይም በጥቅል ለመጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋናውንና ኮፒውን በተናጠል በማሸግ ቢሮ ቁጥር 10 ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያስገቡት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ሲሆን ሲፒኦ በባንክ የተረጋገጠ መሆን አለበት
- ጨረታው በ16ኛዉ ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታላችን ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር አካተው ማቅረብ ያለባቸው ሰነዶች የሚከተሉት ናቸው
ሀ. ከሚቀርቡት ዕቃ ጋር የተዛመደና በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድና የገቢዎች የምዝገባ የምስክር ወረቀት።
ለ. የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ለ15 ቀን ይሸጣል።
ሐ. ከፌዴራል ሀገር ውስጥ ገቢ ወይም ከክልሎች ግብር ሰብሳቢ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ወቅታዊ የግብር ግዴታዎችን የተወጡና በጨረታው መካፈል የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ አቅርቦት የምስክር ወርቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
መ. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ቲን /TIN/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በከፊልም ወይም በሙሉ መጫረት ይችላሉ።
ሠ. ተጫራቾች የሚያስዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ /CPO/ መጠን በጨረታ መመሪያ ላይ የተገለጸ ሲሆን ሲፒኦውን ከኦርጂናል ሰነድ ወይም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከጨረታው ሰነድ ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ረ. ተጫራቾች በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ የድርጅታቸውን ማሕተም እና ፊርማ ማስቀመጥ አለባቸው። ያልተመታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
ሰ. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ሸ. ጨረታውን ያሸነፈው አካል ከቢሮ ጋር ውል በመፈራርም በተፈራረመው ውል መሠረት ዕቃውን ማቅረብ ግዴታ አለበት።
ለተጨማሪ መረጃ ከዚህ በታች በተጠቀሰው ስልክ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ስልክ ቁጥር:- 09 13 25 93 45
የመልካ ኦዳ አጠቃላይ ሆስፒታል
