በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በወላይታ ዞን የሚገኘው የዘላቂ የቤተክርስቲያን ደን አያያዝ የክልል ፕሮግራም ፕሮጀክት ጽ/ቤት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ቦሌ መድኃኒያለም አቅራቢያ ባለው የኮሪያ ወንዝ ላይ የጎርፍ መከላከያ ድጋፍ ግንብ ሥራ እና በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ አረካ ከተማ ሻሎው ዌል፣ ሶላር ፓምፕ፣ ታንከር እና የውሃ ማደያ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መሠረት ደረጃቸው 4 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የውሃ የግንባታ ፈቃድ ያላቸውንና የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያቀርቡ ተወዳዳሪዎችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
በወላይታ ዞን የሚገኘው የዘላቂ የቤተክርስቲያን ደን አያያዝ የክልል ፕሮግራም ፕሮጀክት ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በወላይታ ዞን የሚገኘው የዘላቂ የቤተክርስቲያን ደን አያያዝ የክልል ፕሮግራም ፕሮጀክት ጽ/ቤት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ቦሌ መድኃኒያለም አቅራቢያ ባለው የኮሪያ ወንዝ ላይ የጎርፍ መከላከያ ድጋፍ ግንብ ሥራ እና በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ አረካ ከተማ ሻሎው ዌል፣ ሶላር ፓምፕ፣ ታንከር እና የውሃ ማደያ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መሠረት ደረጃቸው 4 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የውሃ የግንባታ ፈቃድ ያላቸውንና የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያቀርቡ ተወዳዳሪዎችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
- ደረጃቸው WWC 4 እና ከዚያም በላይ ያላቸውና ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፣ የመንግስት ግብር የከፈሉና ጨረታ እንዲወዳደሩ የሚያስችል ታክስ ክሊራንስ የሚያቀርቡ፤ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ሰርቲፊኬት፣ ቫት፤ ቲን፣ እና ሌሎች አሰፈላጊ ማስረጃዎችን ማቅረብ የሚችሉ
- ከዚህ በፊት ለሠሩት ሥራ ተዛማችነትና ተመጣጣኝነት ያለው ከውሃ ጋር የተገናኘ ሥራ ቢያንስ 2 የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ የሚያቀርቡ!
- ጠቅላላ ሥራውን በ60 ቀናት አጠናቀው የሚያስረክቡ!
- ለሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ ከስሌት /arithmetic check/ በኋላ የሚታይ 2 በመቶ እውቅና ካለው ባንክ በሲፒኦ /በባንክ ጋራንቲ የጨረታ ማስከበሪያ (bid bond) ማቅረብ የሚችሉ
- የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ወላይታ ሶዶ በአቡነ ተ/ሃይማኖት ገዳም ግቢ ከሚገኘው የፕሮጀክቱ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የሞሉትን ዋጋ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን (ቴክኒካል እና ፋይናንሻል) በታሸገ ኤንቨሎፕ ለየብቻው እስከ 10ኛው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ የፕሮጀክቱ ጽ/ቤት ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በእለቱ/በ10ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት በፕሮጀክቱ ጽ/ቤት መገኘት በሚፈልጉ ተጫራጮች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። 10ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
- ፕሮጀክቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡ ስልክ 0923477808
ወላይታ ሶዶ
