Tender Detail

Tender Details

  • Company የአቶ ቴዎድሮስ ተፈራ የመኪና ኪራይ ንግድ ድርጅት
  • Address ወሎ ሰፈር ተባበርበርታ ሕንፃ 7ኛ ፎቅ እና አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ መናኸሪያ አጠገብ ሸዋ ዳቦ ጀርባ ገባ ብሎ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-4-70-71-07
  • Website
  • Deadline29 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price1000.00
  • Bid Security20%
  • opening date2025-08-29 00:00:00
  • Categories Vehicle , Used Items

የአቶ ቴዎድሮስ ተፈራ የመኪና ኪራይ ንግድ ድርጅት በሆኑት አትላንቲክ እና TTCR እንዲሁም የአቶ ወንደወሰን ቅጣው መኪና ኪራይ አግልገሎት ድርጅት በሆኑት GIRAR እና የBK በመባል የሚታወቁት ድርጅቶች ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ባሉበት ሁኔታ በድርጅቶቹ ጋራዥ ውስጥ ልዩ ቦታ ቃሊቲ መናኸሪያ ሸዋ ዳቦ ጀርባ በጨረታ አወዳድረው ለመሸጥ ይፈልጋሉ፡፡

የአቶ ቴዎድሮስ ተፈራ የመኪና ኪራይ ንግድ ድርጅት


 

ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችና ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ

ለመሸጥ በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአቶ ቴዎድሮስ ተፈራ የመኪና ኪራይ ንግድ ድርጅት በሆኑት አትላንቲክ እና TTCR እንዲሁም የአቶ ወንደወሰን ቅጣው መኪና ኪራይ አግልገሎት ድርጅት በሆኑት GIRAR እና የBK በመባል የሚታወቁት ድርጅቶች ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ባሉበት ሁኔታ በድርጅቶቹ ጋራዥ ውስጥ ልዩ ቦታ ቃሊቲ መናኸሪያ ሸዋ ዳቦ ጀርባ በጨረታ አወዳድረው ለመሸጥ ይፈልጋሉ፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም የታደሠ መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ተሽከርካሪዎችን ከላይ በተጠቀሰው ቦታ በመሄድ መመልከት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የሚገዙትን ተሸከርካሪ ለእያንዳንዱ ጨረታ ያስገቡበትን ዋጋ ሃያ በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሣጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ የመገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ኦርጅናል (ሲፒኦ) እንዲሁም በለነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይኖርበታል።
  4. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መኪኖቹ በሚገኙበት አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ መናኸሪያ አጠገብ ሸዋ ዳቦ ጀርባ ይከፈታል። ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
  5. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው ከ 7 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለየድርጅቶቹ ገቢ ይደረጋል።
  6. በጨረታው የተሸነፈ ተወዳዳሪ ጨረታው ለአሸናፊ ከተገለፀ ከ21 ቀን የሥራ ቀናት በኋላ ያሲያዙት 20% ሲፒኦ መውሰድ ይችላሉ።
  7. የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል።
  8. የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ የማይመለስ 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) ነው።
  9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ተሸከርካሪውን በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው።
  10. የጨረታ ሰነድ መሸጫ ቦታ አዲስ አበባ ወሎ ሰፈር ተባበርበርታ ሕንፃ 7ኛ ፎቅ እና አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ መናኸሪያ አጠገብ ሸዋ ዳቦ ጀርባ ገባ ብሎ ነው።
  11. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በቀጥታ ስልክ ቁጥር 011-4-70-71-07 በሞባይል 09-61-30-52-27/09 30-17 76 34 /0929- 90 54 77 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
  12. ድርጅቱ በማንኛውም ምክንያት ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. ለአንድ ተሽከርካሪ ዋጋ ማቅረቢያ ለአንድ ተሸከርካሪ ብቻ ተብሎ ይቅረብ።
  14. በጨረታ ሰነድ ላይ በሚቀርበው ፖስታ ላይ የተሸከርካሪው ኮድ እና ሠሌዳ መጻፍ አለበት።
  15. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሱት ደንብና ሁኔታ አስገዳጅ ናቸው።

                                                                                             ድርጅቶቹ

 

Save Tender