Tender Detail

Tender Details

  • Company ኡቡንቱ ቤተሰብ አቀፍ የልጆች ድጋፍ የበጎ አድራጎት ማህበር
  • Address አምቦ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ውስጥ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0912053398
  • Website
  • Deadline21 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security3%
  • opening date2025-08-21 00:00:00
  • Categories Accounting & Auditing

ኡቡንቱ ቤተሰብ አቀፍ የልጆች ድጋፍ የበጎ አድራጎት ማህበር ከ2024 እስከ 2026 የሂሳብ ሰነዱን በጨረታ አወዳድሮ በውጭ ኦዲት ማስመርመር ይፈልጋል።

ኡቡንቱ ቤተሰብ አቀፍ የልጆች ድጋፍ የበጎ አድራጎት ማህበር


 

የኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/18

 

ኡቡንቱ ቤተሰብ አቀፍ የልጆች ድጋፍ የበጎ አድራጎት ማህበር በአምቦ ዪኒቨርሲቲ መምህራንና ሰራተኞች በጎ ፈቃድና ተነሳሽነት በጥቅምት 11/007 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ በምዝገባ ቁጥር 3343 ተመዝግቦ ፈቃድ ያገኘ እና ፈቃዱንም እስከ 2023 ያደሰ ድርጅት ነው። ማህበሩ ከ2024 እስከ 2026 የሂሳብ ሰነዱን በጨረታ አወዳድሮ በውጭ ኦዲት ማስመርመር ይፈልጋል።

በመሆኑም የስራ ዘርፉ የሚመለከታችሁ ተጫራቾች ማህበሩ ባዘጋጀው የመወዳደሪያ ሰነድ መሰረት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የማህበሩ የስራ ቦታ አምቦ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ውስጥ መሆኑን አውቃችሁ በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ የኦዲት አገልግሎት ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. በኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ መስሪያ ቤት የተመዘገቡና ሕጋዊ የኦዲት ሥራ ፈቃድ ያላቸው ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር መክፈያ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. በሌሎች ተመሳሳይ ድርጅቶች /NGO/ ላይ የሰሩበትን የስራ ልምድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  3. ለሂሳብ ምርመራ አገልግሎት ለስራው ከሚጠይቁት ዋጋ ለጨረታ ማስከበሪያ 3% በሲፒኦ ወይንም በጥሬ ገንዘብ በደረሰኝ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራች ድርጅቱ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 3 የተዘረዘሩትን መረጃዎች እና ለሥራው ያቀረበው ዋጋ እንዲሁም ሥራውን አጠናቆ የሚያስረክብበትን ጊዜ በመጫረቻ ሰነዱ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት አየር ላይ ውሎ ነሐሴ 15 ቀን 2017 ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ በኡቡንቱ ቤተሰብ አቀፍ የልጆች ድጋፍ በጎ አድራጎት ማህበር ዋና ቢሮ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው ነሀሴ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 5፡30 ይከፈታል።
  6. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ የኦዲት አገልግሎት ድርጅቶች የጨረታ ሰነዱን ብር 100.00 በመክፈል መግዛት አለባቸው ፡፡
  7. ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡
  8. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0912053398 / 0923112919 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።

 

ኡቡንቱ ቤተሰብ አቀፍ የልጆች ድጋፍ የበጎ አድራጎት ማህበር

 

 

Save Tender