የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2018 የበጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Adama Hospital Medical College (የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ)
ለአንደኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2018 የበጀት ዓመት:-
- ለግቢ ውስጥ መድኃኒቶች እና የህክምና ዕቃዎች
- ለኮሚኒቲ ፋርማሲ መድኃኒቶች እና
- የፈርኒቸር እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ትችላላችሁ።
- የ2017 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ በዘርፉ ያላችሁ።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆኑ መረጃ ማቅረብ የሚችል።
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ፅ/ቤት በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ ።
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ ገዥ መ/ቤት ድረስ በራሳቸው ወጪ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ኮፒና ኦሪጅናል ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማሸግ አለባቸው።
- ስርዝ ድልዝ ያለው፤ የማይታይ የጨረታ ሰነድ ወይም የዋጋ ዝርዝር ተቀባይት የለውም።
- ጨረታውን ከአሸነፈ በኋላ የውል ማስከበሪያ የአሸነፈበትን ዋጋ 10% ማስያዝ የሚችል።
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከኮሌጁ ግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ከፍል ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ለመድኃኒቶች በእያንዳንዱ ጨረታ 500 /አምስት መቶ ብር/ እና ለፈርኒቸር እቃዎች 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ አለባቸው።
- የመድኃኒቶች እና የህክምና እቃዎች ጨረታው የሚከፈተው በ20/12/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- የኮሚኒቲ ፋርማሲ መድኃኒቶች ጨረታው የሚከፈተው በ21/12/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- የፈርኒቸር እቃዎች ጨረታው የሚከፈተው በ21/12/2017 ዓ.ም ከቀኑ 9:30 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚሞሉትን ዋጋ በመስሪያ ቤቱ ሰነድ ብቻ ላይ መሆን አለበት።
- ጨረታ ማስከበሪያ
- ለግቢ ውስጥ መድኃኒቶች እና የህክምና እቃዎች እና በኮሚኒቲ ፋርማሲ መድኃኒቶች ለየ ብቻ 30,000 (ሰላሳ ሺህ ) ብር
- ለፈርኒቸር እቃዎች 20,000 (ሃያ ሺህ) ብር በ"CBE, CBO, እና በSinqee" ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
አዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ
