Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Tourist Trading Enterprise (የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት)
  • Address 22 Mazoriya, Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 011-6-61-09-95
  • Websitehttps://www.ette.com.et/
  • Deadline25 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security100,000.00 /አንድ መቶ ሺሀ ብር/
  • opening date2025-08-25 00:00:00
  • Categories Vehicle , Used Items

የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት ንብረት የሆኑ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

Ethiopian Tourist Trading Enterprise (የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት)


 

የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 01/2018

 

የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት ንብረት የሆኑ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

 

ተ.ቁ

የተሽከርካሪው ዓይነት

የሚይዘው የሰው ብዛት

ተሽከርካሪዎቹ የሚገኙበት ቦታ

የጨረታ መዝጊያ ቀን

የጨረታ መክፈቻ ቀን

1

Nissan Station Wagon

7

 

 

 

 

አያት አደባባይ ፊት ለፊት በሚገኘው የድርጅቱ ቅርንጫፍ እና ቦሌ ካርጎ አጠገብ በሚገኘው የድርጅቱ ግቢ

 

 

 

 

ነሐሴ 19/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት

 

 

 

 

ነሐሴ 19/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት

2

Suzuki Alto

5

3

Nissan Pick up

5

4

Nissan Pick up

5

5

Nissan Pick up

5

6

TOYOTA Pick up

5

7

8 MITSUBISHI Pick up

5

8

Bishoftu Pick up

5

9

10 MITSUBISHI Carry boy

5

10

11 Nissan Minibus

5

11

Nissan Minbus

10

12

Bishoftu Mide bus

30

13

Mercedes Van

2

14

TOYOTA Automobile

5

15

FIAT Truck

1

16

FORK LIFT

 

 

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆነው ሠነዱ ለመግዛት ሲመጡ  ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሠነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት 22 ማዞሪያ በሚገኘው የድርጅቱ ዋናው መ/ቤት የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ከፍለው የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ከነሐሴ 15 ቀን እስከ ነሐሴ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
  4. ተሽከርካሪው ቀደም ሲል ያልተከፈለ የቦሎ እና የጉምሩክ ቀረጥ ግብር ወጪ ካለው ድርጅታችን የሚሸፍን ሲሆን የስም ማዘዋወሪያ፣ የትራንዚት እና ሌሎች ወጪዎች ግን በገዥው ይሸፈናል፡፡
  5. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የሚገዙት ተሽከርካሪ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺሀ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሣጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የጨረታ የመገምግሚያ መስፈርት፣ ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ሲፒኦ/ እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
  7. የጨረታ ሣጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ፣ ንብረት አስተዳደርና ቴክኒክ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀ በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግሥት ገቢ ይደረጋል፡፡
  9. ድርጅቱ ያወጣውን ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡
  10. አሸናፊ ተጫራች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ተሸከርካሪውን በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው።
  11. አሸናፊ ተጫራች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ተሽከርካሪውን በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
  12. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0116 62 24 23 ወይም 0914341342 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት

 

 

Save Tender