የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ለንፋስ ስልክ ላፍቶ ሳይት ጋሻ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ የመስኮት እና ሰገነት ኮፒንግ (sill and coping) በብሔራዊ ግልዕ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን
ጨረታ ማስታወቂያ
ለንፋስ ስልክ ላፍቶ ሳይት ጋሻ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ የመስኮት እና ሰገነት ኮፒንግ (sill and coping) በብሔራዊ ግልዕ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መሰፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታ እንዲሣተፉ ይፈልጋል።
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚገልፅ ሰረተፊኬት (TAX CLEARANCE CERTIFICATE) በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN NO/ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፊኬት በአቅራቢነት የተመዘገቡ (Supplier list) መሆኑን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ ቂርቆስ ክ/ከተማ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ላንድማርክ ሆስፒታል ጎን በሚገኘው በፋውንዴሽኑ ዋና መ/ቤት በመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ግዥ ዳይሬከቶሬት ግዢ ቡድን በስራ ሰዓት በመቅረብ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ) በመክፈል ሠነዱን ማግኘት ይችላሉ።
- ጨረታው በ16ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋውንዴሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ቴከኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ የሚከፈት ሲሆን 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል። የተጠየቀው የቴክኒክ መስፈርት ተቀባይነት ያገኘ እና ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ አሸናፊ ይሆናል። የበለጠ መረጃ በጨረታው ሰነድ ስለሚገለፅ የጨረታው ሰነድ በተገቢ መንገድ ማንበብ የተጫራቹ ሃላፊነት ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ የፋይናንሽያልና የቴክኒክል ሰነድ ለየብቻ በታሽገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ ዋስትና 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ ወይም የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ቴክኒካል ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ማስከበሪያ ሆነ የጨረታ ሰነዱ መግዢያ ከላይ ከተገለፀው ውጪ ፋውንዴሽኑ የማያስተናግድ መሆኑን ተጫራቾች ማወቅ ይጠበቅባቸዋል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ከገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡-
ከቄራ ወደ ሜክሲኮ በሚወስደው መንገድ ላንድማርክ ሆስፒታል ጎን
ስልክ ቁጥር፡- 011-5-57-27-34
መከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን
