የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በአዲስ አበባ ኤርፖርት በኩል ለሚያስመጣቸው ለተለያዩ የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች፣ ማከፋፈያ ጣቢያዎች እና ማስተላለፊያ መስመሮች የሚያገለግሉ እቃዎችን የአስተላላፊነት (የትራንዚት) አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ እና ልምድ ካላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power)
የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት
የጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር EEP/ST
NCB/01/2018
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በአዲስ አበባ ኤርፖርት በኩል ለሚያስመጣቸው ለተለያዩ የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች፣ ማከፋፈያ ጣቢያዎች እና ማስተላለፊያ መስመሮች የሚያገለግሉ እቃዎችን የአስተላላፊነት (የትራንዚት) አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ እና ልምድ ካላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች ሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድህረ-ገፅ (e-GP) ላይ የተመዘገቡ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ጊዜ የጨረታ ሰነድ እንዲሸጥላቸው የጨረታ መለያ ቁጥሩን እና የግዥውን አይነት በመግለጽ፤ በሚመለከተው ኃላፊ የተፈረመ እና የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ወጪ የሆነ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
3. በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝርሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል።
4. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታ ብረት ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ህንፃ ቁጥር-11 1ኛ ፎቅ በሚገኘው ገንዘብ ተቀባይ ቢሮ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል እና የጨረታ ሰነዱን ህንፃ ቁጥር-9 1ኛ ፎቅ ግዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 201 በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች ለተለያዩ የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች፤ ለማከፋፈያ ጣቢያዎች እና ለማስተላለፊያ መስመሮች የሚያገለግሉ እቃዎችን የአስተላላፊነት(የትራንዚት) አገልግሎት ግዥ የቴከኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ላይ የጨረታ ቁጥር EEP/ST/NCB/01/2018 የሚል ምልከት በማድረግ ከታች በተቀመጠው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
|
ሎት |
Description
|
የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ
|
የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት
|
የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት
|
|
1 |
የአስተላላፊነት (የትራንዚት)አገልግሎት ግዥ |
7,500.00(ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር |
ነሐሴ 19 ቀን 2017 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 |
ነሐሴ 19 ቀን 2017 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡30 |
6 ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-558-06-27 መደወል ይችላሉ።
7. ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፤
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
