ማህበረ ሰባዊያን ከ2017 እስከ 2019 ላሉት 3 የበጀት ዓመታት የሚቆይ የሂሳብ ምርመራ (አዲት) ሥራ በተፈቀደለት የውጭ አዲተር የሂሳብ መዝገቡን ለማስመርመር (ኦዲት ለማስደረግ) ይፈልጋል።
ማህበረ ሰብዓዊያን
የጨረታ ማስታወቂያ
ማህበረ ሰባዊያን ከ2017 እስከ 2019 ላሉት 3 የበጀት ዓመታት የሚቆይ የሂሳብ ምርመራ (አዲት) ሥራ በተፈቀደለት የውጭ አዲተር የሂሳብ መዝገቡን ለማስመርመር (ኦዲት ለማስደረግ) ይፈልጋል።
በመሆኑም ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ኦዲተሮች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- ከኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦር (AABE) ሂሳብ ለመመርመር የሚያስችል የሙያ ፈቃድ ያገኘና የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሠርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፤
- በሀገሪቱ ሕግ መሠረት የኦዲት ሥራ ለመስራት የሚያስችል ወቅታዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ/ች
- የታከስ መለያ ቁጥር (TIN) ያለው/ያላት
- ተጫራቾች የአገልግሎት ክፍያ የዋጋ ዝርዝር ጠቅላላ ዋጋቸውን ታክስን ጨምሮ እና ስራውን ሰርተው የሚያጠናቅቁበትን ጊዜ ማለትም የሂሳብ ምርመራውን አጠናቀው ዘገባውን (Report) የሚያስረከቡበትን ጊዜ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎችና ዝርዝር ሁኔታዎችን በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ በማህበሩ ዋና ጽ/ቤት በመቅረብ ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ7ኛው ቀን ተዘግቶ በማግስቱ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ ከዚህ በታች በተቀመጠው የማህበራችን አድራሻ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- ከኤድናሞል ወደ ሃያሁለት በሚወስደው መንገድ ከአደይ አበባ ስታዲየም ፊት ለፊት፣ ንግድ ባንክ ያለበት ህንጻ (ኮዚ ህንጻ) 1ኛ ፎቅ ፣ ቢሮ ቁጥር B፣ አዲስ አበባ
ስልክ ቁጥር፡- +251-974-08-21-83 ወይም +251-911-55-95-26
አዲስ አበባ
ማህበረ ሰብዓዊያን
