ድርጅታችን ኡም ዙበይዳ የበጎ አድራጎት ድርጅት /Umm Zubayda Charity Organization/ የ2017 በጀት ዓመት ሂሳብ ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል።
ዑም ዙበይዳ የበጎ አድራጎት ድርጅት
የሂሳብ ኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ኡም ዙበይዳ የበጎ አድራጎት ድርጅት /Umm Zubayda Charity Organization/ ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት በሰርተፍኬት ቁጥር 7062 ህዳር 20/2016 የበጎ አድራጎት ስራ እንዲሰራ ፍቃድ ተሰጥቶት በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ ሲሆን የ2017 በጀት ዓመት ሂሳብ ኦዲት ለማስደረግ ስለምንፈልግ ተገቢው
- ንግድ ፍቃድ ያላቸው
- በሙያ ብቃትና ሕጋዊነት ታውቀው በመንግስት የተመዘገቡ፤
- የዘመኑን ግብር ከፍለው በ2017 በጀት ዓመት ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፤
- የኦዲቲንግ የስራ ልምድ ያላቸው፤
- የተመሰከረለት የሂሳብ አዋቂዎች ሰርተፍኬት ያላቸው፤
- የታክስ መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን አለባቸው።
አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ግዜ አንስቶ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በነዚህ ከታች በተጠቀሱት አድራሻ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
አድራሻ:- ጦርሀይሎች የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 406 ሆላንድ ኢምባሲ አጠገብ
ስልክ ቁጥር +251911167601
ዑም ዙበይዳ የበጎ አድራጎት ድርጅት
