የቻሎት ቤዛ ሪል ስቴት አክሲዮን ማህበር የ2017 በጀት ዓመት የማህበሩን ሒሣብ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል።
የቻሎት ቤዛ ሪል ስቴት አክሲዮን ማህበር
የውጭ ኦዲተር ጨረታ ማስታወቂያ
የቻሎት ቤዛ ሪል ስቴት አክሲዮን ማህበር የ2017 በጀት ዓመት የማህበሩን ሒሣብ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል። ስለሆነም ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ ማሰራት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የምታሟሉ እና መወዳደር የምትፈልጉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ።
- ሕጋዊ ፍቃድ እና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት፣
- የዘመኑን ግብር የከፈለ እና የሥራ ልምድ ማስረጃ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሠርተፍኬት እና የታደሰ ፍቃድ፣
- ሥራውን ለመስራት የሚፈጅበትን ጊዜ እና ዋጋ እንዲሁም መረጃዎችን ማቅረብ የሚችል እነዚህን ማስረጃዎች በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ መርካቶ ከምዕራብ ሆቴል በስተጀርባ አካባቢ በቻሎት የገበያ ማዕከል ሕንጻ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 504 ገቢ እንድታደርጉ እናስታውቃለን፡፡ የጨረታው ምዝገባ በተጠናቀቀ በቀጣይ የሥራ ቀን ጠዋት 3፡00 ሰዓት ላይ የጨረታው ሣጥን የሚዘጋ ይሆናል፡፡ የጨረታው ምዝገባ በተዘጋ በቀጣይ ባለው ቅዳሜ ቀን ከጠዋቱ 4፡00- 6፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ቢሮ 504 ይከፈታል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0112-29-70-80 ወይም 0967-35-62-62-18 ሊደውሉ ይችላሉ፡፡
የቻሎት ቤዛ ሪል ስቴት አክሲዮን ማህበር
