Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
  • Address ወልቂጤ ከተማ ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-3300112
  • Website
  • Deadline23 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Securityለፅህፈት መሣሪያዎች ብር 50,000 /ሃምሳ ሺ ብር/፣ ለተለያዩ ማሽን ቀለሞች ብር 30,000 /ሰላሳ ሺ ብር/፣ ለፅዳት ዕቃ 25,000 /ሃያ አምስት ሺ ብር/
  • opening date2025-08-23 00:00:00
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials , Paint

በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በዞኑ ለሚገኙ ሴ/መ/ቤ/ቶች አገልግሎት የሚውሉ የፅህፈት መሣሪያዎች፤ የተለያዩ ማሽን ቀለሞች እና የፅዳት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ


 

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 1/2017-2018

 

በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በዞኑ ለሚገኙ ሴ/መ/ቤ/ቶች አገልግሎት የሚውሉ፡-

  1. ሎት 1 የፅህፈት መሣሪያዎች
  2. ሎት 2 የተለያዩ ማሽን ቀለሞች
  3. ሎት 3 የፅዳት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸው፣
  4. የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  5. የግዢው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሰውንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ ዓይነት፣ የአምራቹን ስም፤ የተመረተበትን ዓ.ም በዝርዝር ከዋናው ጨረታ ሰነድ ጋር መያያዝ አለበት፣
  8. ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና ሲጠየቅ ማቅረብ አለበት፣
  9. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለፅህፈት መሣሪያዎች ብር 50,000 /ሃምሳ ሺ ብር/፣ ለተለያዩ ማሽን ቀለሞች ብር 30,000 /ሰላሳ ሺ ብር/፣ ለፅዳት ዕቃ 25,000 /ሃያ አምስት ሺ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት CPO፣ ቢድ ቦንድ በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ስም ተዘጋጅቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  10. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 – 3 የተጠቀሱትን የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ በመክፈል ሰነዱን ከጉራጌ ዞን ፋ/መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/የስራ ሂደት ሁለተኛ ፎቅ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፣
  11. ማንኛውም ተጫራች ዕቃውን ጉራጌ ዞን ፋ/መምሪያ ወልቂጤ ከተማ ድረስ ለማቅረብ የሚያስችል ዋጋ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ በማለት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በጥንቃቄ ታሽጐ ይህ ማስታወቂያ በ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ጉራጌ ዞን ፋ/መምሪያ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/የሥራ ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት አለባቸው።
  12. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጐ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ አዳራሽ በይፋ ይከፈታል።
  13. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-3300112 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

ማሳሰቢያ ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የምታቀርቡ 90 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን እንዳለበት እንገልፃlን።

 

በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

 

Save Tender