የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ሕግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በ 09/12/2017 ዓ/ም በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ሕግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በ 09/12/2017 ዓ/ም በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት መግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት በተጫራች ስም የማይመለስ 100 (መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየትና እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በሟሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን የእቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣልዎት የምትፈልጉት የእቃ ናሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን በስልክ ቁጥር 022-224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እንዲመጣልዎት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
የጨረታ መስፈርቶች:
- ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት ፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንሰ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክሰ እንቅሰቃሴያቸውን ለታክስ ማዕከሉ ያሳወቀበት፣ በቅርብ ጊዜ የተሰጠ የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀን 09/12/2017 ዓ/ም ባሉት ቀናት በግልፅ እስከ ጠዋቱ 3፡45 እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ በዚሁ ቀን እስከ ረፋዱ 5፡00 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይችላሉ።
- በግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (cpo) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5% እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ ብር) በባንክ አሠርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (እሰኬጁል) መሠረት በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ፡፡
|
ተ.ቁ |
የጨረታ ቦታ |
የጨረታ ዓይነት |
ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች |
የዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
2 |
ቃሊቲ ጉምሩክ |
ግልጽ ሐራጅ |
ጫማዎች፣ አልባሳት፣ ኮስሞቲክስ፣ የመኪና መለዋወጫ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ፣ ምግብ ነክ፣ የስፖርት እቃዎች፣ የእጅ ሰዓት፣ መነፅር እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች |
ለግልፅ ጨረታ እስከ ዓርብ 09/12/2017 ጠዋቱ 3፡45 |
ለግልፅ ጨረታ በ09/12/2017 ዓ/ም ጠዋቱ 3፡45 እና ለሐራጅ ጨረታ እስከ 5፡00 |
- የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
- ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋሰትና ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የሥራ ቀናት ውሰጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖርበታል፡፡
- ከላይ በተ.ቁ.7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙትን ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሜ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
- ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በጉምሩክ ኮሚሽን የአዋሽ ቅ/ጽ/ቤት
