Tender Detail

Tender Details


በኢሉባቦር ዞን የዲዱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዘመን በወረዳ ስር ለሚገኙ መስሪያ ቤቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በኢሉባቦር ዞን የዲዱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በኢሉባቦር ዞን የዲዱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዘመን በወረዳ ስር ለሚገኙ መስሪያ ቤቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

1. የፅሕፈት መሳሪያዎች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች እና የጽዳት ዕቃዎች፣

2. ኤሌክትሮኒከስና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች (ፈርኒቸሮች)፤

3. የደንብ ልብሶችና የስፌት ዋጋ፤

4. የመኪና ጎማና የሞተር ሳይከል ጎማ፣

5. የማሽን ኪራይ ማለትም ዶዘር፣ ግሬደር፣ ሩሎ ዳምትራክ ስንቫተር፤

በዚሁ መሠረት በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል።

1. በዘርፉ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የቲን ነምበር ያላቸውና የ2017 ዓ.ም የመንግስት ግብር ከፍለው ያጠናቀቁና ንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

3. የሚቀርበው ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ (ኦሪጅናልና ኮፒ) ሆኖ ሠነድ ስርዝ ድልዝ ከሆነ ተቀባይነት አይኖረውም።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ማቅረብ (በዲዱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አካውንት ቁጥር 1000056003987 ገቢ አርገው የባንከ ስሊፕ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

5. አሸናፊ ተጫራቾች ለመልካም ሥራ አፈጻጸም ወይም የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10% በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን አንስተው ባሉት ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ በኢሉባቦር ዞን ከዲዱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ከፍል የአንዱ ሠነድ ዋጋ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ከፍለው መግዛት ይችላሉ፡፡

7. ጨረታው የሚከፈተው ለፅሕፈት መሳሪያዎች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች እና የጽዳት ዕቃዎች በ 21/12/2017 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ጀምሮ ሲሆን ለኤሌክትሮኒከስ እና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች (ፈርኒቸሮች) በ22/12/2017 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት ጀምሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ የሚከፈት ሆኖ ተወካዮች ህጋዊ የውከልና ደብዳቤና ሰነድ ማቅረብ አለባቸው። ለደንብ ልብሶች፣ ለደንብ ልብስ ስፌት ዋጋ፡ ለቴከኒከና ሙያ ሥልጠና የሚያገለግሉ መሣሪያዎች፤ የመኪና ጎማ እና የሞተርሳይክል ጎማ በ23/12/2017 ዓ.ም ከ4፡00 ሰዓት ጀምሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በገልጽ ይከፈታል።

8. የዕቃው ማስረከቢያ ቦታ የዲዱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ሆኖ መገጣጠሚያ፤ ማስጫኛና ማውረጃ ትራንስፖርት ወጪ በአጠቃላይ የሻጭ ግዴታ ናቸው።

9. ከፍያ የሚደረገው የተጠየቁ ዕቃዎች በአጠቃላይ ገቢ ሲሆኑና እንደ ኤሌክትሮኒክስ ያሉ ዕቃዎች በባለሙያ ታይተው ተቀባይነት ሲያገኙ ብቻ ክፍያው ይደረጋል።

10. በሌላ ተጫራቶች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።

11. የዕቃ ብዛት ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል።

12. የተጠየቀው ዕቃ በተጠየቀው ሰነድ መሠረት ሞልተው ማቅረብ እና ደረጃውን የጠበቀ ዕቃ ማቅረብ አለበት፤ ያልተጠየቀውን ዕቃ ቢሮ ካዘጋጀ ሰነድ ውጭ በሌላ/ ካቀረበ እንዲሁም ደረጃውን ያልጠበቀ ዕቃ ከሆነ ተቀባይነት አይኖረውም።

13.አሸናፊ ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዕቃዎች ከፋከቱር ጋር አዘጋጅተው ማቅረብ የሚችሉ (ዕቃዎቹና ፋከቱር) መለያየት የለበትም።

14. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዕቃዎች በተለይ የደንብ ልብስ እንዲመረጥ ዘንድ ማለትም ለናሙና የተለያዩ ከሦስት ዓይነት ያላነሰ ጨርቃ ጨርቅ እንዲሁም ጫማ ከሦስት ያላነሱ ማቅረብ አለባቸው።

15.መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።

ማሳሰቢያ፡- ዶዘሮን በተመለከተ ወረዳችን ዝናባማ ስለሆነ ጨረታውን ለምትወዳደሩ ተጫራቾች ሰነዱን ገዝታችሁ ቢሮው በጠራችሁ ሰዓት ቀርባችሁ የምትወዳደሩ መሆኑን በእከብሮት እናሳውቃለን።

ለበለጠ መረጃ:- 09-13-37-75-82/ 09-17-83-09-27

የኢሉባቦር ዞን የዲዱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

Save Tender