Tender Detail

Tender Details


የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ምዕራብ (ጅማ) ዲስትሪክት የጥራት ደረጃ የሚያሟሉ፣ የምግብ ጨው፣ የጸጉር ቅባት፣ አጃክስ ሳሙና፣ የገላ መታጠቢያ ሳሙና (CES44፡2013) የተማሪዎች ቦርሳ፣ እርሳስ፣ እስክርቢቶ፣ A-4 የፕሪንተር ወረቀት (CES: ISO 216:2016) ነጭ ጤፍ፣ የሀገር ውስጥ ሩዝ፣ ምጥን (ለወተት ምርት መኖ)፣ የስንዴ ገለባ (ፉሩሽካ)፣ ለከብት እርባታ የባቴላ ገለባ ምርቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት በሚቆይ የማዕቀፍ ግዥ ስልት መግዛት ይፈልጋል።

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ምዕራብ (ጅማ) ዲስትሪክት


 

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ምዕራብ (ጅማ) ዲስትሪክት

1. ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 02/017

 

ድርጅታችን በኢትዮጵያ የወጣውን የጥራት ደረጃ የሚያሟሉ፣ የምግብ ጨው፣ የጸጉር ቅባት፣ አጃክስ ሳሙና፣ የገላ መታጠቢያ ሳሙና (CES44፡2013) የተማሪዎች ቦርሳ፣ እርሳስ፣ እስክርቢቶ፣ A-4 የፕሪንተር ወረቀት (CES: ISO 216:2016) ነጭ ጤፍ፣ የሀገር ውስጥ ሩዝ፣ ምጥን (ለወተት ምርት መኖ)፣ የስንዴ ገለባ (ፉሩሽካ)፣ ለከብት እርባታ የባቴላ ገለባ ምርቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት በሚቆይ የማዕቀፍ ግዥ ስልት መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች:

  1. በዘርፉ የታደስ ንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የብቃት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት፤ የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው የሚያረጋግጥ ክሊራንስ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሠርተፍኬት ያላቸው መሆን ይገባቸዋል።
  2. ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ጅማ ሄርማታ መንቲና ቀበሌ ሸዋ ሆቴል ፊት ለፊት አካባቢ ከሚገኘው ከዲስተሪክቱ ጽ/ቤት የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ግዥና ሽያጭ ቡድን ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ እና ለመልካም ሥራ አፈፃፀም በጨረታ መመሪያው ላይ በተቀመጠው መሰረት ለየምርቶቹ የተጠየቀውን መጠን በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ/ሲ.ፒ.ኦ ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
    1. ከዚህ ቀደም ለሌላ ጨረታ የተያዘ ሲ.ፒ.ኦን ለዚህ ጨረታ እንዲያዝ ማድረግ አይቻልም።
    2. ተጫራቾች በጨረታ መመሪያው ላይ የሚቀመጡትን ህጎች በሙሉ የማክበር ግዴታ አለባቸው።
  4. የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውንና ከላይ ከተጠቀሱት ህጋዊ ሠነዶች ጋር በታሽገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጅናል እንዲሁም አንድ ኮፒ በማድረግ እስከ ነሀሴ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 8፡00 ሰዓት ድረስ ጅማ ሄርማታ መንቲና ቀበሌ ሸዋ ሆቴል ፊት ለፊት አካባቢ ከሚገኘው ዲስተሪክቱ ጽ/ቤት የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ግዥና ሽያጭ ቡድን ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  5. ጨረታው በተመሳሳይ ቀን (ነሀሴ 7 ቀን 2017 ዓ.ም) ከረፋዱ 8፡30 ተጫራቾች በተገኙበት ይከፈታል።

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ እንዲሁም ለማህበረሰቡ ይጠቅማሉ ያላቸውን ውሳኔዎች የመወሰን መብቱ የተጠበቀ ነው።

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 047-111-03-22/9966

 

Save Tender