ኒዩትሪሽን ፎር ኤዱኬሽን ኤንድ ዴቨሎፕመንት (Nutrition 4 Education & Development - N4ED) የተባለው የሲቪል ማህበረሰብ አገር በቀል ድርጅት የ2017 ዓ/ም የድርጅቱን ሒሳብ በጨረታ አወዳድሮ ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡
Nutrition 4 Education & Development - N4ED (ኒውትሪሽን ፎር ኤዱኬሽን ኤንድ ዴቨሎፕመንት)
የጨረታ ማስታወቂያ
ኒዩትሪሽን ፎር ኤዱኬሽን ኤንድ ዴቨሎፕመንት (Nutrition 4 Education & Development - N4ED) የተባለው የሲቪል ማህበረሰብ አገር በቀል ድርጅት ከነሀሴ 26 ቀን 2008 ዓ/ም ጀምሮ በላይሰንስ ቁጥር 3687 በኢፌዴሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተመዝግቦ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል። ድርጅቱ በየዓመቱ በሰኔ 30 ሂሳቡን የሚዘጋ ሲሆን፣ የ2017 ዓ/ም የድርጅቱን ሒሳብ በጨረታ አወዳድሮ ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ለመጫረት የምትፈልጉ የኦዲት ድርጅቶች (Audit firms) ከዚህ በታች የተጠቀሱት በማሟላት አንድትወዳደሩ እንጋብዛለን፦
- የአዲተር የሙያ ማረጋገጫ፣
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣
- የዘመኑን ግብር ስለመክፈሉ መረጃ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣
- ከኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ (A.A.B.E) ፈቃድ፡፡
ለመጫረት የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች የምትሰሩበትን ዋጋና የሚያስፈልገውን የጊዜ መጠን የሚገልጽ ፕሮፖዛል በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርጋችሁ ሳር ቤት (ከአደምስ ፓቪሎን በታች ባለው ጸሃይ ኢንሹራንስ ያለበት ህንጻ ላይ ሁለተኛ ፎቅ) በሚገኘው ቢሮአችን ይህ ማስታወቂያ በወጣበት በ10 የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት ትችላላችሁ።
ኒውትሪሽን ፎር ኤዱኬሽን ኤንድ ዴቨሎፕመንት
