ካሌብ ሰርቪስ ፋርመርስ ሃውስ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር አዲስ አበባ ዋናው መስሪያ ቤት የሚገኙ የተለያዩ የትራክተር፣ የኤክስካቬተር፣ የግብርና ተቀፅላ ማሽነሪ መለዋወጫዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ካሌብ ሰርቪስ ፋርመርስ ሃውስ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር - KS/001/2017
ካሌብ ሰርቪስ ፋርመርስ ሃውስ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር አዲስ አበባ ዋናው መስሪያ ቤት የሚገኙ የተለያዩ የትራክተር፣ የኤክስካቬተር፣ የግብርና ተቀፅላ ማሽነሪ መለዋወጫዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ/ ብር በመግዛት ዋጋቸውን በመሙላት ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ዘወትር በሥራ ስዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚቆየው ጋዜጣው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ሲሆን በ 11ኛው ቀን 4፡00 ተከፍቶ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የተለያዩ መለዋወጫ እቃዎች ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው እቃዎች ድርጀቱ ባወጣው የመነሻ ዋጋ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሰነድ ከገዙ በኋላ የድርጅቱ መጋዘን በመቅረብ የእቃዎቹን ናሙና በአካል ማየት ይችላሉ።
- አሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ ያሸነፉባቸውን እቃዎች ዋጋ ከፍሎ በ15 ቀናት ውስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ:- አዲስ አበባ ፣ አቃቂ/ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 5፣ ሸገር ዳቦ ፊት ለፊት አውሮራ ሆቴል አጠገብ
ስልክ ቁጥር +251 11 439- 36-75/ +251 988- 27-58-63/+251 920-49-79-38/
ካሌብ ሰርቪስ ፋርመርስ ሃውስ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
