Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)
  • Address ሳሪስ አቦ ፋፋ የምግብ አክሲዮን ጎን 200 ሜትር ገባ ብሎ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114709095
  • Websitehttps://ethioagri.com/
  • Deadline12 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security2
  • opening date2025-08-12 00:00:00
  • Categories Furniture And Furnishing , Carpets And Curtains

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የ2017/18 በጀት ዓመት የቢሮ ፈርኒቸሮች እና የወለል ምንጣፍ ዕቃዎችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ዝርዝር እስፔስፍኬሽን መሰረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)


 

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር ኢግ.ሥ.ኮ./ብግጨ/01/2017

 

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የ2017/18 በጀት ዓመት የቢሮ ፈርኒቸሮች እና የወለል ምንጣፍ ዕቃዎችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ዝርዝር እስፔስፍኬሽን መሰረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ፤ የቫት ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ የምዝገባ ሠርተፊኬት (TIN) እንዲሁም ከገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አቦ ፋፋ ፋብሪካ አጠገብ የቀድሞው እርሻ መሣሪያዎችና ቴክኒክ አገልግሎት አ.ማ ግቢ የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 110 ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ የጠቅላላውን ዋጋ 2% በሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ (Unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታው ዋጋ ለ60 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል፡፡

ጨረታው የሚዘጋው ነሐሴ 6 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሆኖ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ከጠዋቱ 4፡30 ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ የመክፈቻ ስነሥርዓት ይከናወናል፡፡

ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-

ስልክ 0114709095/0114-423608

ፋክስ 0114-421312

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

 

Save Tender